ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ጉዳት/አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ተገቢውን ካሣ ከፍሎ በውክልና የተረከባቸውን ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ የተሸከርካሪ አካሎችና በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Nile-Insurance-1

Overview

  • Category : Vehicle Foreclosure
  • Posted Date : 01/23/2023
  • Phone Number : 0114421499
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 02/03/2023

Description

ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 142/2015)

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

  • ጉዳት/አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ተገቢውን ካሣ ከፍሎ በውክልና የተረከባቸውን ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ የተሸከርካሪ አካሎችና በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የተሽከርካሪ የስም ማዛወሪያ፣ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ግብርና ሌሎች ዕዳዎችና ወጪዎች ቢኖሩ በአሸናፊው የሚሸፈኑ ይሆናል፡፡

የተሽከርካሪ የስም ዝውውር በገዢ ምክንያት ከስድስት ወር በላይ ቢቆይ በዚህ ምክንያት ለሚመጣ ችግር ኩባንያችን ኃላፊነት አይወስድም፡፡

አሸናፊ ተጫራች የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

  1. ንብረቶቹ የሚገኙበት የኩባንያው ሪከቨሪ አድራሻ፡-
  • ገላን ሪከቨሪ               ፡  ገላን ኖክ ማደያ ፊት ለፊት

ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በሥራ ሰዓት ሄዶ በማየት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍሎ መውሰድ ይችላል፡፡

የጨረታ መነሻ ዋጋ 15% ቫት ያላካተተ መሆኑን እየገለጽን፤ ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን የእያንዳንዱን ምድብ እቃ ዋጋ (ቫት ሳይጨምር) በጨረታ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት ለእያንዳንዱ ምድብ እቃ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን 20% (ሃያ ከመቶ) በኩባንያው ስም በተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የኢንሹራንስ ቦንድ ጋር በኤንቨሎፕ በማሸግ እስከ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የኩባንያው ዋና መ/ቤት በሚገኝበት ጎተራ ምድር ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል፡፡

ማሳሰቢያ፡- አሸናፊ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ 15% ቫት የሚጨመር መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ጨረታው  ጥር 20 ቀን 2015 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎተራ በኩባንያው ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ሙሉ በሙሉ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ከሚገዙበት ዋጋ ጋር ይታሰባል፡፡ ተጫራቾች ለተጫረቱበት ንብረት አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በአሥር ቀናት ውስጥ ክፍያውን አጠናቀው ንብረቱን ባያነሱ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል፡፡

ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ

በስልክ ቁጥር 011-442-14-99/09-11-82-05-76/ በመደወል መጠየቅ ይችላል፡፡

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ