ኔፕ ፕላስ በሲቪል ማህበረሰብ አጭር የአንድ ደቂቃ የቴሌቪዥን እና ራዲዮ መልዕክት ዝግጅት እና ስርጭት አገልግሎት ብቁ ከሆኑ የኤልክትሮኒክስ ሚዲያዎችን አወዳድሮ ማሰራትይፈልጋል፡

network-of-networks-of-hiv-positives-logo-1

Overview

 • Category : Public Relations & Public Address Systems
 • Posted Date : 07/23/2022
 • Phone Number : 0116591616
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/12/2022

Description

አጭር የቴሌቪዥን እና ራዲዮ መልዕክት ዝግጅትና ስርጭት ጨረታ

ኔፕ ፕላስ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን መዝገብ ቁጥር 1483 የተመዘገበ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን በትኩረት ከሚያከናውናቸው የጤና እና የልማት ሥራዎች መካከል አንዱ ኤች አይ ቪ አድስ ስረጭትን መግታት ሲሆን ሥራውንም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ ይፈጽማል፡፡  

ድርጅታችን የኤች አይ ቪ ምርመራ፣መድሃኒት በአግባቡ መውሰድ እና የቫይረሱን መጠን ለመቆጣጠር እንዲያመች በማህበረሰቡ ዘንድ ፍላጎትን ለመጨመር አጭር የአንድ ደቂቃ የቴሌቪዥን እና ራዲዮ መልዕክት ዝግጅት እና ስርጭት አገልግሎት ብቁ ከሆኑ የኤልክትሮኒክስ ሚዲያዎችን አወዳድሮ ማሰራት ስለምንፈልግ ይህን የአጭር መልዕክት በሦስት ቋንቋዎች(አማርኛ፤አፋን ኦሮሞ፤ትግርኛ) አሰርቶ ማሰራጨት ስለፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጋብዟል፡፡      

 • አገልግሎቱን ከሚያቀርበው ድርጅት የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታዎች
 • ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣TIN ሰርተፍኬትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበት የምስክር ወረቀት ሊኖራቸው ይገባል፤
 • ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችለውን ደብዳቤ ከገቢዎች ማቅረብ የሚችል
 • የብሮድካስት ባለሥልጣን ፈቃድ ያለው፤
 • ከተመሳሳይ ድርጅቶች ጋር በመስራት ልምድ ያለውና በዘርፉ ቢያንስ ከ 5 ዓመት በላይ የሠራ፤
 • በኤች/አይ/ቪ.ኤድስ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ላይ የሠራና ከሰራቸው ስራዎች ውስጥ ቢያንስ አራት ስራዎችን ከምስጋና ሰርተፊኬትጋር ማቅረብ የሚችል፤
 • ሥራውን የሚያከናውንበትን ጊዜ በግልጽ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፤
 • የጥራት ደረጃዎችን የጠበቁ የምስልናየድምፅ ቀረፃዎችን የሚያከናውን፤የሰው ሀብት የማቴሪያል ዝርዝር ያሟላ፤ለዚህም ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችል፤
 • ተጫራቾች ድርጅቱ ያወጣውን የጨረታ መመሪያን በሙሉ መከተል አለባቸው፤
 • ከላይ ከተገለጹት ሁኔታዎች ውስጥ አንዱን አለማክበሩ ከጨረታው ውድቅ ያደርጋል፤
 • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ሰዓት ሜክሲኮ አደባባይ አከባቢ በሚገኘው ድርጅታችን መግዛት ይችላሉ፤
 • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/ሲፒኦ.ማስያዝ አለባቸው፤
 • የፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ፕሮፖዛል 1 ኦርጅናል እንዲሁም 1 ኮፒ በሠም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው፤
 • የጨረታው ሰነድ ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ህንጻ 5ኛ ፎቅ፤ ድርጅታችን የፋይናንስና አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 405 ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመቅረብ ማስገባት ይኖርበታል፤
 • ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ 8፡30 ላይ ይከፈታል፤
 • ተጨራቾች ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር (+251)011-659-16-16/1919 ማግኘት ይችላሉ፤
 • ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

ማስታወሻ፡- የፕሮዳክሽን ስራውን እና የስርጭቱን ስራ በተናጠል መወዳደር ይቻላል፡፡