ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለጥበቃ ሰራተኞች አገልግሎት የሚውል ካፖርት ሕጋዊና የስራ ልምድ ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Nib-International-Bank-logo-3

Overview

 • Category : Textiles/ Fabrics & Wearing
 • Posted Date : 08/28/2021
 • Phone Number : 0115512650
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/17/2021

Description

የጥበቃ ካፖርት ግዥ ግልጽ ጨረታ

የጨረታ መለያ ቁጥር ንብ/10/2014

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለጥበቃ ሰራተኞች አገልግሎት የሚውል ካፖርት ሕጋዊና የስራ ልምድ ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ ዝርዘር መግለጫ መለኪያ ብዛት
1 የጥበቃ ካፖርት በቁጥር 3,100
 1. ጨረታው በባንኩ የግዢ መምሪያ ላይ በተጠቀሰው የግልጽ ጨረታ ሂደት መሰረት ይከናወናል፡፡
 2. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ደብዳቤ፣ የግብር ከፋይነት ሠርቲፍኬት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋናው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00/ብር ሁለት መቶ/ በመክፈል ከነሐሴ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት እና ከ7፡00-11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 50,000.00(ብር ሃምሳ ሺህ ) ቢያንስ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ቅድመ ሁኔታን ያላካተተ በባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ  ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ከዋናው የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይቻላል፡፡
 5. አድራሻ፡ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 26ኛ ፎቅ ሰንጋ ተራ አከባቢ፣ ግዢ ዋና ክፍል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115512650/0115504452 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጥበቃ ካፖርት ናሙና/Sample/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አብሮ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተካተቱትን መመሪያዎች በጥንቃቄ ማንበብና ማሟላት ይገባቸዋል፡፡ ይህንን ሳይከተል የተዘጋጀ ሰነድ ውድቅ ሊደረግ ይችላል፡፡
 8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋናውን እና አንድ ኮፒ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተራ ቁጥር 5 ስር በተጠቀሰው አድራሻ እስከ መስከረም 07 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡15 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው መስከረም 07 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት 9፡15 ሰዓት ተዘግቶ መስከረም 07 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 5 ስር በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የደረሰ መወዳደሪያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ  የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ..

ስልክ ቁጥር 0115512650/0115504452 

ፋክስ 011 5 622448