ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በያስገነባው ዘመናዊ የህንጻ ተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ክፍሎችን ለደንበኞቻችን ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

Nib-International-Bank-logo-2

Overview

  • Category : Rent
  • Posted Date : 04/17/2021
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 05/07/2021

Description

የፍላጎት መግለጫ ጨረታ ማስታወቂያ!

 ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አዲስ ወደ አስገነባነው ዘመናዊና ሰማይ ጠቀስ ሕንጻ የመዛወር ሂደቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

ሁሌም ለደንበኖቹ ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የሚታወቀው ባንካችን እነሆ የታታሪነት ተምሳሌት የሆነውን፣ ዘመናዊና ማራኪ ህንጻ በመዲናችን አዲስ አበባ ገንብቶ ሪቫን ለማስቆረጥ ተዘጋጅቷል፡፡

ባንካችን በከፍተኛ ገንዘብ ያስገነባው ይኸው ባለ 37 ወለል ሰማይ ጠቀስ ዘመናዊ ሕንጻ ለከተማዋ ልዩ ውበት፣ ለአካባበው ደግሞ ግርማ ሞገስ ማላበሱን ብዙዎች መስክረውለታል፡፡

በዚህ ግዙፍና ዘመናዊ የህንጻ ጥበብ ባረፈበት ህንጻችን ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ክፍሎችን ለደንበኞቻችን ለማከራየት ዝግጅታችንን ያጠናቀቅን በመሆኑ ፍላጎት ያላችሁ ድርጅቶችም ሆናችሁ ግለሰቦች ፍላጎታችሁን የሚገልጽ ሰነደ በማቅርብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እየገልጽን የፍልጎት መግለጫ ሰንዶቻችሁን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ውስጥ ደንበል ሲቲ ሴንተር በሚገኝው ዋና መ/ቤት  4ኛ ፎቅ ፋሲሊቲስና ሜንቴናንስ መምሪያ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ከባንካችን ጋር ይስሩ! የዘመናዊ ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሁኑ!

ይሠሯል፣ ከልብ እንደ ንብ!

ንብ ኢንተርናሽና ባንክ