ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሠረት 2,309 የሆኑ አክሲዮኖች፣ የሚያወጡ አክሲዮኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Bank Related
 • Posted Date : 09/24/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/12/2021

Description

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ

አክሲዮኖችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሠረት የውጭ ሀገር ዜግነት ከያዙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን ብዛታቸው 2,309 የሆኑ አክሲዮኖች፣ የአንዱ አክሲዮን ዋጋ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ሆኖ ጠቅላላ ዋጋቸው ብር 1,154,500.00 (አንድ ሚሊየን አንድ መቶ ሃምሳ አራት ሺ አምስት መቶ ብር) የሚያወጡ አክሲዮኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

 1. የአንድ አክሲዮን የጨረታ ወይም የመወዳደሪያ መነሻ ዋጋ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ነው)፡፡
 2. ተጫራቾች በጨረታው መግዛት የሚችሉት አነስተኛ የአክሲዮን ብዛት በቁጥር 200 ሲሆን ከዚህ በታች የሆኑ አክሲዮኖች ለመግዛት የሚቀርብ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
 3. ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ወይም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች የተያዙ ድርጅቶች ወይም የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች ወይም ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች ባለአክሲዮኖች የተያዙ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍና መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን አክሲዮኖች ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ከጨረታው ቀን በፊት ራስ አበበ አረጋይ መንገድ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ንግድ ስራ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 25ኛ ፎቅ በባንኩ ፋይናንስ እና አካውንትስ መምሪያ በመገኘት ከመስከረም 18 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሠነዶችን በመውሰድ መሙላትና በሰም በታሸገ አንቨሎý በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት 25ኛ ፎቅ በሚገኘው ቼክ ክሊራንስና አክሲዮን አስተዳደር ዋና ክፍል ማስገባት አለባቸው፡፡
 5. የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች ወይም ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ ተወላጅ በሆኑ የውጭ ዜጎች ባለአክሲዮኖች የተያዙ ድርጅቶች መግዛት የሚችሉት በውጭ ምንዛሪ ማለትም በዶላር ወይም በዩሮ ወይም በፓውንድ ብቻ ሲሆን፤በከፊል የኢትዮጵያ ተወላጅ በሆኑ የውጭ ዜጎች የተያዙ ድርጅቶች እንደ አክሲዮናቸው መጠን በውጭ ምንዛሪ የሚከፈል ይሆናል፡፡
 6. ጨረታው ጥቅምት 3 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ራስ አበበ አረጋይ መንገድ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ንግድ ስራ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 25ኛ ፎቅ በባንኩ ፋይናንስ እና አካውንትስ መምሪያ ይከፈታል፡፡
 7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ አክሲዮኖቹን የሚጫረቱበትን ዋጋ ¼ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ፍላጎታቸውን ከሚገልፁበት ሠነድ ጋር በሰም በታሸገ ኢንቨሎý ውስጥ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 8. ተጫራቾች አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
 9. ተጫራቾች ዜግነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፖስፓርት ወይም መንጃ ፈቃድ ወይም ተቀባይነት ያለው ሌላ ማስረጃ ኮፒ እንዲሁም ድርጅቶች ከሆኑ የባለአክሲዮኖቹን ዜግነት የሚያረጋግጥ የመመስረቻ ጽሑፍ ወይም ተቀባይነት ያለው ሰነድ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 10. ዜግነት የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
 11. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
 12. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በአምስት (5) የሥራ ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ ለሚመለከተው አካል ገቢ ይሆናል፡፡
 13. ማንኛውም በጨረታው አፈፃፀም ላይ ሊፈጠር የሚችል አለመግባባት ቢከሰት አግባብነት ባለው በሌሎች ሕጐችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ሕጐች ተፈፃሚነት አላቸው፡፡
 14. ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ