ኖህ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ያገለገሉ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Vehicle Sale
  • Posted Date : 06/11/2021
  • Phone Number : 0114424627
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 06/24/2021

Description

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ኖህ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ያገለገሉ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች በአክሲዮን ማህበሩ የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር መመሪያ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀናት ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀን ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የሚገዙትን ተሽከርካሪ ዋጋ ከነቫቱ እንዲሁም በባንክ የተረጋገጠ ብር የ30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

ጨረታው ለጨረታ ማቅረቢያ በተወሰነው የመጨረሻ ቀን ተዘግቶ በሚቀጥለው የሥራ ቀን አራት ሰዓት ላይ (4፡00 ሰዓት) ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቁ ነው፡፡

አድራሻ፡- ኖህ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር ዋናው መስሪያ ቤት

ከዩኒቨርሳል ቆዳ ፋብሪካ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር 0114 42 46 27/0114 42 55 21

0911 20 77 07