አለማ ካውዳይስ የእንስሳት መኖ ኃ/የተወ/የግል /ማህበር ለምርት ማሸጊያ የሚሆኑ ከታች  በሠንጠረኝ የቀረቡትን የፒፒ ከረጢቶችን (PP Bags) ከአምራች ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Alema-koudius-feeds-plc-logo

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 09/03/2021
 • Phone Number : 0114330662
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/15/2021

Description

ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

አለማ ካውዳይስ የእንስሳት መኖ ኃ/የተወ/የግል /ማህበር ለምርት ማሸጊያ የሚሆኑ ከታች  በሠንጠረኝ የቀረቡትን የፒፒ ከረጢቶችን (PP Bags) ከአምራች ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ/ቁ ዓይነትና መግለጫ መለኪያ ብዛት
1 የፒፒ ከረጢቶች (PP Bags) 72×115 ሳሜ 110 ግራም ቁጥር 330,000
2 የፒፒ ከረጢቶች (PP Bags) 61×110 ሳሜ 90 ግራም ቁጥር 670,000

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ አምራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

 1.  ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር  የከፈሉ
 2. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመግዛት ቅፁ በሚፈቅደው መሰረት ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 1. ተጫራቾች  ማናቸውንም  የመንግስት  ወጪና    ትራንስፖርትን  ጨምሮ  ድርጅቱ  ድረስ   በማቅረብና  በቁጥር የሚያስረክቡበትን የአንድ ፒፒ ከረጢት (PP Bag) ሂሳብ በማስላት የጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ሰነድ በመሙላት የድርጅቱን  ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተምና ፊርማ አስደግፎ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ከነሃሴ 30 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 6 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30  ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት  ላይ ታሸጋል፡፡ ከዚያም በዚያኑ  ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት  በድርጅቱ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ  ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም  ጨረታው በተባለው ቀንና  ሰዓት ይከፈታል ፡፡
 1. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 1 % ማስያዝ አለበት፡፡
 2. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በሁለት ቀናት ጊዜ ውስጥ ድርጅቱ ጽ/ቤት በመቅረብ ውል በመዋዋልና ውሉ ሲያበቃ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው 1% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
 1. የጨረታው አሸናፊ  ውል ከተዋዋለበት ቀን  ጀምሮ በውሉ  በተጠቀሱት የስራ  ቀናት  ጊዜ ውስጥ ለድርጅቱ ማስረከብ አለበት፡፡
 2. ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስረከበሪያ ገንዘብ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
 3. ሌሎች  ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው፡፡
 4. ድርጅቱ የተሻለ  አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፤ አለማ ካውዳይስ መኖ ኃ/የተ/የግል ማህበር

ደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ቀበሌ 01  የቤት ቁጥር 3190  (ዝቋላ መንገድ ከአሜሪካን ብረታ ብረት ማቅለጫ አጠገብ)

ስልክ ቁጥር +251 11 433 06 62/+251 11 433 52 42