አልሳም ኃ/የተ/የግል ማህበር ያገለገሉ እና በጥሩ ሁኔታ የሚገኙ ተሸከርካሪዎችን በጨረታ በባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Vehicle Sale
  • Posted Date : 10/15/2022
  • Phone Number : 0111557774
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 10/27/2022

Description

 አል ሳም ኃ/የተ/የግል ማህበር

ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች  የጨረታ ማስታወቂያ

አልሳም ኃ/የተ/የግል ማህበር ያገለገሉ እና በጥሩ ሁኔታ የሚገኙ ተሸከርካሪዎችን በጨረታ በባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

1) ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ከጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 17ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ሜክሲኮ ጨለቅለቅ አልሳም  ህንጻ ፓርኪንግ ውስጥ በሥራ ሰዓት  በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡

2)  ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሜክሲኮ በሚገኘው ጨለቅለቅ አልሳም ሽያጭ መምሪያ መውሰድ ይቻላል፡፡

3)  ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የተሸከርካሪ ዓይነት የጨረታ የመነሻ ዋጋቸውን 20% (ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለ አልሳም ኃ/የተወ/የግል ማህበር (AL SAM PLC) በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4) ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ በመፃፍ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሜክሲኮ በሚገኘው ጨለቅለቅ አልሳም ህንጻ ሽያጭ መምሪያ ለ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5)  ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ አሸናፊ ለሆኑት ለሚገዙት ተሸከርካሪ ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን ተሸናፊ ለሆኑት ያስያዙት የባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ተመላሽ ይደረጋል፡፡

6)  ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው፡፡

7) የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ሃሙስ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ  ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሜክሲኮ በሚገኘው ጨለቅለቅ አልሳም ህንጻ ሽያጭ መምሪያ በግልጽ ይከፈታል፡፡

8) አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ6 (ስድስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረታቸውን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል፡፡

9) የጨረታ አሸናፊው ከጨረታው በኋላ ያሉትን የስም ማዘዋወሪያ ወጪዎች ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል፡፡

10) በተሽከርካሪዎቹ ላይ ማንኛውም ዓይነት የመንግስት ዕዳ ቢኖር ሻጭ ይከፍላል፡፡

11) ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 1 55 77 74 , 0996 99 43 43 ወይም 0949 33 46 78 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡