አልፋ የትምህርትና ሥልጠና አክስዮን ማሕበር በባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሚያስገነባው ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ህንጻ /Mixed use building/ የህንጻ ተቋራጭን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Alpha-Educational-And-Training-Logo

Overview

 • Category : Construction Service & Maintenance
 • Posted Date : 07/08/2021
 • Phone Number : 0114669238
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/10/2021

Description

  የህንጻ ግንባታ ሥራ ግልጽ ጨረታ

    አልፋ የትምህርትና ሥልጠና አክስዮን ማሕበር በባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሚያስገነባው ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ህንጻ /Mixed use building/ የህንጻ ተቋራጭን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

     ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉና ደረጃ BC-1 ወይም GC-2 እና  ከዚያ በላይ የሆነ የህንጻ ተቋራጮች በሙሉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው
 2. የዘመኑን ግብር የከፈለ
 3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
 4. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
 5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሲያስገቡ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን መስረጃዎች ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ሥራውን በገባው ውል መሰረት አጠናቆ ማስረከብ የሚችል
 7. የሚሰሩ ሥራዎችን አይነትና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል
 8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 100.00/አንድ መቶ/ በመክፈል አልፋ የትምህርትና ሥልጠና አ/ማ ፈይናንስ ቢሮ ቁጥር 201 ወይም አልፋ ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር 01 ከሐምሌ 05 ቀን 2013 እስከ ነሐሴ 4 2013 ዓ.ም ማግኘት ይችላሉ
 9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ዋጋ 2 % በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (cpo) ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጂናልና አንድ ፎቶ ኮፒ የተክኒክና ፋይናንሺያል በጥንቃቁ በታሸገ ፓስታ አልፋ የትምህርትና ሥልጠና አክስዮን ማሕበር የጠቅላላ አገልግሎት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በአካል በመቅረብ  ወይም አልፋ የትምህርትና ሥልጠና አ/ማ በፓስታ ሳጥን ቁጥር 12759 በመላክ  በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርበታል፡፡
 11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በቢሮ ቁጥር 01 ነሐሴ 05 ቀን2013 ዓ.ም በ4 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ

አክስዮን ማሕበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገዎት አልፋ የትምህርትና ሥልጠና አክስዮን ማሕበር ዋናው መ/ቤት አራት ኪሎ ወ.ወ.ክ.ማ ጎን ቢሮ ቁጥር 201 ወይም አልፋ ባሕር ዳር የትምህርት መንደር  በአካል በመገኘት ወይም በሥልክ ቁጥር 0114669238 አ.አ ወይም 0582221062 ባሕርዳር ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤፤

አልፋ የትምህርትና ሥልጠና አክስዮን ማሕበር                                                                                      

Send me an email when this category has been updated