አልፋ የትምህርትና ስልጠና አክስዮን ማህበር የባለአክስዮኖች 27ኛው ዓመታዊ መደበኛ እና 7ኛው ድንገተኛ ጠቅላላ ጐባኤ ጥሪ
Overview
- Category : Announcement
- Posted Date : 11/20/2022
- Source : Reporter
- Closing Date : 10/26/2022
Description
27ኛው ዓመታዊና 7ኛው ድንገተኛ የባለአክስዮኖች የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
የአልፋ የትምህርትና ስልጠና አክስዮን ማህበር የባለአክስዮኖች 27ኛው ዓመታዊ መደበኛ እና 7ኛው ድንገተኛ ጠቅላላ ጐባኤ እሑድ ሕዳር 11 ቀን 2ዐ15 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡ዐዐ ጀምሮ አዲስ አበባ ግሎባል አካባቢ በሚገኘው የማህበሩ ሕንፃ የስብሰባ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የማሕበሩ ባለአክስዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በስብሰባው ላይ እንዲገኙ የማሕበሩ የዲሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
የአክስዮን ማህበሩ 27ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
1ኛ. የ2ዐ14 በጀት ዘመን የስራ ክንውን ሪፖርትና የ2ዐ15 በጀት ዘመን ዕቅድና በጀት ማዳመጥ
2ኛ. በወጭ ኦዲተሮች የሚቀርበውን የበጀት ዘመኑን የሒሳብ ሪፖርት ማድመጥ
3ኛ. በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ
4ኛ. የ2ዐ14 በጀት ዓመት የትርፍ ክፍፍል ላይ ተነጋግሮ መወሰን
5ኛ. የዲሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልና ከትርፍ ድርሻ ተከፋይ ከሚሆነው አበል ላይ ተወያይቶ መወሰን
6ኛ. የውጭ ኦዲተሮች ባቀረቡት የክፍያ ማስተካከያ ላይ ተወያይቶ መወሰን
7ኛ. የእለቱን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ
የአክስዮን ማህበሩ 7ኛው ድንገተኛ የባለአክስዮኖች ጉባኤ አጀንዳ
1ኛ. በማህበሩ የካፒታል ምዝገባ ላይ የተፈጠረውን ስህተት ተወያይቶ ስለማረም
ማሳሰቢያ
- በስብሰባው ላይ ለመገኘት የማይችል ባለ አክስዮን ከስብሰባው ዕለት ቢያንስ 13 ቀናት በፊት ማህበሩ ያዘጋጀውን የውክልና መስጫ ሰነድ አራት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው የአክስዮን ማህበሩ የአክስዮን አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 2 ቀርቦ በመፈረም ሌላ ሰው መወከል ይችላል፡፡
- በውል አዋዋይ የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ ማስረጃውን ይዞ በመቅረብ በስብሰባው ላይ መሳተፍ ይችላል፡፡
አልፋ የትምህርትና ስልጠና አክስዮን ማህበር የዲሬክተሮች ቦርድ፡፡