አልፋ የትምህርትና ስልጠና አክስዮን ማሕበር በባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሚያስገነባው ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ህንጻ (Mixed use building) የህንፃ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Alpha-Educational-And-Training-Logo

Overview

 • Category : Construction Service & Maintenance
 • Posted Date : 09/03/2021
 • Phone Number : 0114669238
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/27/2021

Description

በድጋሚ የወጣ የህንፃ ግንባታ ሥራ ግልጽ ጨረታ

አልፋ የትምህርትና ስልጠና አክስዮን ማሕበር በባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሚያስገነባው ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ህንጻ (Mixed use building) የህንፃ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉና ደረጃ BC-1  ወይም GC-2 እና ከዚያ በላይ የሆነ የህንጻ ተቋራጮች በሙሉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው
 2. የብቃት ማረጋገጫ
 3. የዘመኑን ግብር የከፈለ
 4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
 5. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሲያስገቡ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ሥራውን በገባው ውል መሰረት አጠናቆ ማስረከብ የሚችል
 8. የሚሰሩ ሥራዎችን አይነትና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል
 9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 2ዐዐ.ዐዐ (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ግሎባል አካባቢ በሚገኘው አልፋ የትምህርትና ስልጠና አ.ማ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 26 ወይም አልፋ በሕር ዳር ቢሮ ቁጥር ዐ1 ከጳጉሜ 01 ቀን 2ዐ13 እስከ መስከረም 16 ቀን 2ዐ14 ዓ.ም ማግኘት ይችላሉ
 10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያያ ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ የቴክኒክና ፋይናንሽያል ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አልፋ የትምህርትና ስልጠና አ.ማ የጠቅላላ አገልግሎት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር G-15 በአካል በመቅረብ ወይም አልፋ የትምህርትና ስልጠና አ.ማ በፖስታ ሳጥን ቁጥር 12759 በመላክ ወይም በተዘጋጀው የጨታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርበታል፡፡
 12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በቢሮ ቁጥር G-15 መስከረም 17 ቀን 2ዐ14 ዓ.ም በ4 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ

አክስዮን ማሕበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገዎት አልፋ የትምህርትና ስልጠና አክስዮን ማሕበር ዋናው መ/ቤት ግሎባል ፊት ለፊት ያለው የአልፋ ዩኒቨርስቲ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር G01 ወይም አልፋ ባሕር ዳር የትምህርት መንደር በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር ዐ11 466 92 38 አ.አ ወይም ዐ58 222 1ዐ 62 ባሕር ዳር ደውለው መጠየቅ ይችላል፡፡

          አልፋ የትምህርትና ስልጠና አክስዮን ማህበር