አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህ/ስ/ማህበር መደበኛ የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 01/11/2023
 • Phone Number : 0930032130
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/14/2023

Description

የስብሰባ ጥሪ

   አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህ/ስ/ማህበር ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም መደበኛ የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ   በሶርአምባ ሆቴል አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ ስለሚያካሂድ አባላት ወይም ህጋዊ ወኪሎች የሆናችሁ በዚሁ ስብሰባ ላይ እንድትገኙ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ከጉባኤው እለት አስቀድሞ አባላት ወይንም ህጋዊ ወኪሎች በማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ   የውክልና ቅጽ እንድትሞሉ እንጠይቃለን፡፡

የስብሰባው አጀንዳዎች

 • ምልዓተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ
 • የጉባኤውን ድምጽ ቆጣሪዎች መሰየም
 • የጉባኤውን ረቂቅ አጀንዳዎች ማጽደቅ
 • የኦዲት ሪፖርት ማድመጥ
 • የስራ አመራር ቦርድ የስራና የሒሳብ ሪፖርት ማዳመጥ
 • የስራ አመራር ቦርድ እና የኮሚቴዎች ምርጫ
 • በቀጣይ የአክሲዮን ማህበር የስራ እንቅስቃሴዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0930032130 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ህብረት ለስምረት!

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር