አማራ ልማት ማህበር (አልማ) ብሪጅ ስቶን ጀማል 7.50*16፤ ያኮሃማ ኤ.ቲ.፤ ብርጅስቶን ኤ.ቲ.265/70አር*15 ጎማዎች በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 08/24/2022
 • Phone Number : 0115512528
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/09/2022

Description

የተለያዩ ብራንዶችና ሳይዝ/መጠን/ ያላቸው ጎማዎች ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉ ህዝብና የልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት በማንቀሳቀስ በትምህርት፣በጤና፣ በመሠረታዊ ሙያ ክህሎትና ስልጠና የስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋጽኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ በመሆኑም ከአባሎቹና ከአጋር ድርጅቶች የሚገኘውን ሀብት በማቀናጀት በመንግስት ያልተሸፈኑ የትምህርት፤ የጤና እና የሥራ እድል ፈጠራ ጉድለቶችን በመሸፈን እየሰራ ይገኛል ፡፡

በዚህም መሰረት አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ብሪጅ ስቶን ጀማል 7.50*16 ብዛቱ 15/አስራ አምስት/፤ ያኮሃማ ኤ.ቲ.5 ብዛቱ 5/አምስት/፤ ብርጅስቶን ኤ.ቲ.265/70አር*15 ብዛቱ 20/ሃያ/፤ 185*70*14 ኤሊውስ ብዛቱ 10/አስር/ እና 185*65*15 አፖሎ ብዛቱ 10/አስር ጎማዎች  በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ     ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፡፡
 1. የግዥ መጠን ብር 50, 000.00 / ሃምሳ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
 2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ የሚቻል ሲሆን ፤የጨረታው ማወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በማያያዝ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ፤ በአስራ አምስተኛው ቀን በ8፡00 ሰአት የጨረታው ሳጥን ታሽጎ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
 5. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
 6. ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አዲስ አበባ ቦሌ ማተሚያ ቤት ጎን አልማ ህንፃ 2ፎቅ ቢሮ ቁጥር 208 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0115512528፤ 0115517886 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡