አማራ ባንክ አ.ማ በጊዜያዊነት ለዋና መ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተጠናቀቀ 2B+G+15 ህንፃ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Amhara-Bank-S.C-

Overview

 • Category : House & Building Purchase
 • Posted Date : 11/05/2022
 • Phone Number : 0115582905
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/29/2022

Description

የህንፃ ግዢ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- አባ/ግክ/083/2022

አማራ ባንክ አ.ማ በጊዜያዊነት ለዋና መ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተጠናቀቀ 2B+G+15 ህንፃ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህንፃዎች ያሏችሁና ለመሸጥ ፍላጐት ያላችሁ ባለንብረቶች ወይም ተወዳዳሪዎች በዚህ ጨረታ እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

/ ህንፃው የሚገኝበት አካባቢ (location)

 • በአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንሺያል፣ኮሜርሺያል እና ቢዝነስ ዲስትሪክት አካባቢ በዋና መንገድ ላይ የሚገኝ መሆን ይኖርበታል፡፡

/ ህጋዊ መስፈርቶች

 • የህንፃውን ህጋዊ ባለቤትና ይዞታ፣ ሙሉ ስምና አድራሻ እንዲሁም የግንባታ ፍቃድ የተሰጠበትን ማቅረብ የሚችሉ፣
 • ህንፃው የሚሸጥበትን ዋጋ በቴክኒካል እና ፋይናንሺያል በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ማቅረብ የሚችሉ፣
 • የቦታው ህጋዊ ይዞታነት በከተማው ማስተር ፕላን የተደገፈ መሆኑን የሚያሳይ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርበታል፡፡
 • ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ህንፃ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ጠቅላላ ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ፤

 1. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሠነዱን ከለገሃር ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በሚወስደው መንገድ መብራቱን እንደተሻገሩ የአመልድ ህንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ግዢና ፋሲሊቲዎች መምሪያ 20ኛ ፎቅ ላይ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብቻ / በባንኩ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
 2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ እስከ ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም.  እስከ 7:30 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ብቻ ነው፡፡
 3. የጨረታው ሰነድ ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በ8፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 4. በውድድሩ ወቅት ባለንብረቶች ሁሉንም ህጋዊ ሰነዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ

 • ለገሀር አካባቢ በሚገኘው የአማራ ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት 20ኛ ፎቅ በግዢና ፋሲሊትስ ማኔጅመንት መምሪያ በአካል በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 0115582905 ወይም 0115584491 በመደወል መረጃ መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

አማራ ባንክ አ.ማ