አማራ ባንክ አ.ማ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎችን የሚያቀርቡ ብቁ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Amhara-Bank-S.C-

Overview

 • Category : Stationery Supplies
 • Posted Date : 08/03/2022
 • Phone Number : 0115584491
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/17/2022

Description

የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር አባ/ግዋክ/062/2014

አማራ ባንክ አ.ማ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎችን የሚያቀርቡ ብቁ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

 • ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ክሊረንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • የጨረታ ሠነዱን ከለገሃር ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በሚወስደው መንገድ መብራቱን እንደተሻገሩ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋሲሊቲዎች አስተዳደር መምሪያ 20ኛ ፎቅ ላይ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ምድር ወለል ላይ በሚገኘው አማራ ባንክ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች ከጨረታው በኃላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ደብዳቤ (ጋራንቲ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ ነሐሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
 • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 አማራ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ግዥ ክፍል 20ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
 • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011558 4491 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
 • ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አማራ ባንክ አ.ማ