አምረፍ ሔልዝ አፍሪካ በኢትዮጵያ (Amref Health Africa in Ethiopia) አለም አቀፍ ግበረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን የሚከተሉትን ያገለገሉ እና ጥገና የሚፈልጉ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Amref-Health-Africa-logo-reportertender-2

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 05/25/2022
 • Phone Number : 0116627851
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/14/2022

Description

ጨረታ ቁጥር 001/2014

የጨረታ ማስታወቂያ

አምረፍ ሔልዝ አፍሪካ በኢትዮጵያ (Amref Health Africa in Ethiopia) አለም አቀፍ ግበረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን የሚከተሉትን ያገለገሉ እና ጥገና የሚፈልጉ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል፡፡

  1. ሎት 1- የኮምፒውተር እቃዎች ሎት 4- ጀነሬተሮች
  2. ሎት 2- የቢሮ መገልገያ እቃዎች /ወንበር፣ ጠረጴዛ እና ወዘተ/ ሎት   5- ሞተር ሳይክሎች
  3. ሎት 3- የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች ሎት 6- ተሽከርካሪዎች

የጨረታውን ሰነድ ስለመግዛት፡ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 በሚከተለው የአካውንት ቁጥር ገቢ አድገው የባንክ ስሊፕ በማቅረብ ሰነዱን ከድርጅቱ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ወጋገን ባንክ/ሻላ ቅርንጫፍ/ የባንክ አካውንት ቁጥር-0075992910104

የአካውንት ሥም- አምረፍ ሔልስ አፍሪካ በኢትዮጵያ

የጨረታው ሰነድ ዋጋ- ብር 150.00

 1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ ሐሙስ ጠዋት (ከ2፡30-6፡30 ፣ ከሰዓት ከ7፡30-11፡00) አርብ (ከ2፡30-6፡30) የሚሸጡትን ያገለገሉ እና ጥገና የሚፈልጉ ተሽከርካሪዎችን ፣ ወንበሮችን፣ ጠረጴዛዎች ሌሎች የቢሮ ቁሳቁሶች አምረፍ ሔልዝ አፍሪካ በኢትዮጵያ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ውስጥ ቀርበው መመልከት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች ሊገዙት ለሚፈልጉት እቃዎች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታው ሰነድ ውስጥ በተዘጋጀው የመጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 15 /በአስራ አምስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ማለትም  አምረፍ ሔልዝ አፍሪካ በኢትዮጵያ ቅጽር ግቢ ውስጥ  በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የተለያዩ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ /የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ/ Amref Health Africa in Ethiopia ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ሲፒኦ/ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ጋር በታሸገ ፖስታ ውስጥ አብሮ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ጨረታው ማክስኞ ሰኔ 7 2ዐ14 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን አሸናፊው ወዲያው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ በጨረታው አሸንፈው ከፍለው ለማይወስዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ቢድቦንድ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡ የጨረታ አሸናፊዎች ያገለገሉ እና ጥገና የሚፈልጉ ወንበሮችን፣ ጠረጴዛዎችና ሌሎች የቢሮ ቁሳቁሶች የማጓጓዣ ወጪዎችንና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎችን ይሸፍናሉ፡፡
 5. በጨረታው ለሚሸነፉት ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ የጨረታ አሸናፊው ሙሉ ክፍያውን እንደፈጸመ የሚመለስላቸው ይሆናል፡፡
 6. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አምረፍ ሔልዝ አፍሪካ በኢትዮጵያ

አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ቦሌ /ከተማ ወረዳ 03 ቦሌ መድኃኒአለም ቤ/ክ ጀርባ ከአቢሲኒያ ሕንጽ ጐን ፣ አምረፍ ሔልዝ አፍሪካ በኢትዮጵያ ቅጥር ግቢ ውስጥ

ስልክ፡ 0116627851 ወይም 0911 1 449 61/0911 165913