አምባሰል ንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ እና የአደጋ መከላከያዎችን አቅራቢዎችን አጫርቶ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Ambasel-Trading-House-Logo

Overview

 • Category : Textiles/ Fabrics & Wearing
 • Posted Date : 07/30/2022
 • Phone Number : 0114666668
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/11/2022

Description

የደንብ ልብስ ጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ እና የአደጋ መከላከያዎችን አቅራቢዎችን አጫርቶ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

 1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ታክስ ክሊራንስ የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑ፣
 2. የደንብ ልብሶችን በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘረዘሩት መሰረት ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆኑ በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ መሆኑ፣
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
 4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አምባሰል ህንፃ ቢሮ ቁጥር 503 ቀርባችሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 50.00 (ሃምሣ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣
 5. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከታወጀበት ከ25/11/2014 ወይም እ.ኤ.አ.01/08/2022 ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ ሲሆን (ለስራ ቀን አቆጣጠር ሲባል ቅዳሜ ከጥዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ያለው ጊዜ የገዥ የስራ ቀን ስለሆነ እንደ አንድ ሙሉ የስራ ቀን ይቆጠራል) ስለሆነም በ10ኛው ቀን በ5/12/2014 ዓ.ም ወይም በ11/08/2022 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ፤ በእለቱ ከቀኑ 8፡30 አ/አበባ የገዥ ዋና መ/ቤት ማለትም አምባሰል ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 ላይ የጨረታ መከፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
 6. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ አምባሰል ንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግ. ማህበር ወሎ ሰፈር አምባሰል ህንፃ ቢሮ ቁጥር 505 ወይም በስልክ ቁጥር 0114666668 / 0114700949   ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አምባሰል ንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር