አምባሰል ንግድ ስራዎች ኃ/የተ/ግ/ማህበር ፒፒ ከረጢት፣ የቃጫ ጆንያ፣ እጣን እና የፋብሪካ ተረፈ ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Other Sale
- Posted Date : 09/03/2021
- Phone Number : 0114700354
- Source : Reporter
- Closing Date : 09/17/2021
Description
Company Name:
አምባሰል የንግድ ስራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር
Ambasel Trading House Pvt. Ltd. Co
Import – Export, Wholesale Distribution& Business Representation)
Doc No.: OF/ATH/030
የጨረታ ማስታወቂያ
አምባሰል ንግድ ስራዎች ኃ/የተ/ግ/ማህበር ፒፒ ከረጢት፣ የቃጫ ጆንያ፣ እጣን እና የፋብሪካ ተረፈ ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላችሁን የታደሰ የዘመኑ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥት እና ተጨማሪ እሴት ታከስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች ለመግዛት የሞሉትን የእቃ አይነት ጠቅላላ ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond በባክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ኦርጅናል የድርጅቱ ማህተም ባለው ከጨረታ ዋጋ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡትን እጣን እና የተለያዩ የፋብሪካ ተረፈ ምርቶችን ናሙና በተመለከተ እጣኑን ባህርዳር በሚገኘው ቅርንጫፍ መጋዘን እና ተረፈ ምርቶችን እና ማዳበሪያዎችን በጐንደር ፕሮሰሲንግ መጋዘን በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል (በእቃው ዓይነት) መግዛት መጫረት የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር የእቃ አይነት እና መጠን የሚገልፅን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው በመውሰድ ሠነዱን ሞልተው በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ በማሸግ ከታች በተገለፁት አድራሻዎች ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጳጉሜ 01 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን ጨረታው በ10ኛ የሥራ ቀን ማለትም በ07/01/2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ የጨረታ ሰነዶች ከቅርንጫፎች ተሰብስበው ወደ ዋናው መ/ቤት የሚመጡበትን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ በ15ኛው የሥራ ቀን ማለትም መስከረም 13/01/2014 ዓ.ም ሀሙስ ጥዋት 4፡00 ሰዓት በሻጭ አድራሻ ማለትም አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ቦታ ኢትዮ-ታይና ወዳጅነት መንገድ አምባሰል ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 ላይ የጨረታ መከፈት ስነ-ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በጨረታ መክፈት ስነ-ስርዓቱ ላይ የተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታውን ዋጋ አያሣጣውም፡፡
- የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሑፍ እንደተገለጸለት እንደታወቀ ያሸነፉበት የእቃ መጠን የመግዣ ዋጋ አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000009223413 በማስገባት በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ማንሳት ይኖርበታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየቅርንጫፎቻችን እና ዋና መ/ቤት በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ ፡- ለተጨማሪ ማብራሪያ አዲስ አበባ በስልክ ቁጥር 0114-70-03-54/0114-66-63-97 ፤ ባ/ዳር በስልክ ቁጥር 09-18-34-00-03፤ ጐንደር 0918-35-00-53/0918/35-00-06 ፤ ደሴ 0-14/31-01-36 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አምባሰል የንንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር