አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር ካምፓኒ ፕሮፋይል፣ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ እና የሬዲዮ ማስታወቂያ ኦዲዮ-ቪዡዋል ፕሮዳክሽኖችን ሕጋዊ የፕሮዳክሽን ካምፓኒዎችን አወዳድሮ በጨረታ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

Ambasel-Trading-House-Logo-3

Overview

 • Category : Entertainment & Docu
 • Posted Date : 08/27/2022
 • Phone Number : 0114666145
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/09/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር ካምፓኒ ፕሮፋይል፣ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ እና የሬዲዮ ማስታወቂያ ኦዲዮ-ቪዡዋል ፕሮዳክሽኖችን ሕጋዊ የፕሮዳክሽን ካምፓኒዎችን አወዳድሮ በጨረታ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የሚገዛው የፕሮዳክሽን ዓይነት ብዛት ሎት የጨረታው ቁጥር
1 ካምፓኒ ፐሮፋይል 01 ሎት-1  
2 የቴሌቪዥን ማስታወቂያ 01 ሎት-2  
3 የሬዲዮ ማስታወቂያ 01 ሎት-3  

የጨረታ ዝርዝር መስፈርት

 1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ተገቢውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
 2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ሰርቲፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ባንክ ጋራንቲ) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከአምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503 ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ እና በwww.2merkato.com ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ዐሥር ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ኦሪጂናል ሰነዶችን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች ለየብቻቸው አሽገው እንደገና ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በማሸግ እንዲሁም በተመሳሳይ መልኩ የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ኮፒ ሰነዶችን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች ለየብቻቸው አሽገው እንደገና ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት አየር ላይ ውሎ በስምንተኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ይዘጋል፡፡ በዚሁ እለትም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አምስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኩባንያው አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 8. የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
 9. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ

ወሎ ሰፈር ኢትዮ-ቻይና የወዳጅነት መንገድ አምባሰል ሕንጻ 4ኛ 5ኛ እና 6ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ

በስልክ ቁጥራችን 0114-66-61-45/0114-66-64-09 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር