አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር ለኩባንያው ሰራተኞች የተለያዩ አልባሳት የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Ambasel-Trading-House-Logo-1

Overview

 • Category : Textiles/ Fabrics & Wearing
 • Posted Date : 06/11/2021
 • Phone Number : 0114700349
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/25/2021

Description

 ለኩባንያው ሰራተኞች የተለያዩ አልባሳት (የደንብ ልብስ) የጨረታ ማስታወቂያ

አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር ለኩባንያው ሰራተኞች የተለያዩ አልባሳት የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

 1. የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያመላክት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው እና በንግድ ዘርፉ የተሰማራ ሰው መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
 2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤
 3. TIN (የንግድ መለያ ቁጥር) ያለው እና ማቅረብ የሚችል፣
 4. ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ያቀረበውን የመጫረቻ ዋጋ 5% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል፣
 5. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ መሙያ ሰነዱን ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሻጭ አድራሻ ማለትም አ/አበባ ቅርንጫፍ ወሎ ሰፈር ቂርቆስ ክ/ከተማ ኢትዮ ቻይና ወዳጅነት መንገድ አምባሰል ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503 በመሄድ መግዛት ይችላሉ፤
 6. ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 7. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣበት ከ06/10/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ (ለስራ ቀን አቆጣጠር ሲባል ቅዳሜ ከጧዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ያለው ጊዜ የአገልግሎቱ ገዥ የስራ ቀን ስለሆነ እንደ አንድ ሙሉ የስራ ቀን ይቆጠራል) ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን ማለትም በ18/10/2021 ዓ.ም ከጧዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጧዋቱ 3፡30 ሰዓት በአገልግሎት ገዥ ዋና መ/ቤት ማለትም አምባሰል ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 ላይ የጨረታ መከፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በጨረታ መክፍት ስነ ስርዓቱ የተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታውን መከፈት ዋጋ አያሳጣውም፡፡
 8. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

አድራሻ፡- ወሎ ሰፈር አምባሰል ሕንፃ ስልክ ቁጥር 0114-70-03-49 ደውሎ የሚፈልገውን ማብራሪያ ማግኘት ይችላል፡፡

አምባሰል ንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር

Send me an email when this category has been updated