አምቦ መዕድን ውሃ አክስዮን ማህበር ዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል ።

Ambo-Mineral-Water-S.c.-Logo-2

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 06/15/2021
 • Phone Number : 0911825651
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/01/2021

Description

ልፅ ጨረታ

አምቦ መዕድን ውሃ አክስዮን ማህበር በኢትዮጵያ የተመዘገበ የአምቦ መዕድን መጠጥ ውሃ አና የለስላሳ መጠጦች አምራች ድርጅት ነው። ድርጅቱ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል ። የተሽከርካሪዎቹ መገኛ ቦታ በቃሊቲ ዋና መስሪያ ቤት ማለትም ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም አቅራቢያ ይገኛል።

የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ አመልካቾች በዚህ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

 1. ማንኛውም ተጫራች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ እና ታክስ መለያ ቁጥር ሊኖረው ይገባል ፡፡
 2. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር ከግዥ ክፍል ብር 200 በመክፈል ማግኘት ይችላሉ ፡፡
 3. ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ መኪና 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል
 4. ሲፒኦ በአምቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማኅበር ስም መዘጋጀት አለበት ።
 5. የታሸጉ የጨረታ ሰነዶች ተመዝግበው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ ሰኔ 25 ቀን 2021 ድረስ በሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው ፡፡
 6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ መኪና ታርጋ ቁጥር እና የተወዳዳሪውን ስም በፖስታው ላይ በመጥቀስና ንግድ ፍቃድ ኮፒ በማያያዝ በሰም በታሸገ ፖሰታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
 7. የቢሮ ሰዓቶች ከሰኞ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከሰኔ 14 እስከ ሐሙስ ሰኔ 24 2021 ከጠዋቱ 02፡30 እስክ ቀኑ 10 ፡30 እና አርብ ሰኔ 25 ቀን 2021 ከጠዋቱ 02:30 እስከ ቀኑ 6:00 ብቻ ነው ፡፡
 8. ተጫራቾች ከአንድ በላይ ለሆኑ ተሽከርካሪዎች መሳተፍ ይችላሉ ፡፡
 9. ተጫራቾች ለተጫራቱት ዋጋ ከቫት በፊት እና ቫትን ለያይተው ማቅረብ አለባቸው ፡፡
 10.  የጨረታ መክፈቻ ቀን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሰኔ 25 2021 እአአ ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ ነው ፡፡
 11. የተረጋገጠ አሸናፊ የአሸነፈበትን የተሽከርካሪ ዋጋ በሁለት ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል ፡፡
 12. አሸናፊው የተሽከርካሪውን ዋጋ ጥሬ ገንዘብ ካስገባ በኋላ በ 10 / አስር / ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተሽከርከሪውን መሰብሰብ አለበት ፡፡ በአሸናፊው ተሽከርካሪው ካልተሰበሰበ አሸናፊው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ ምሽት ብር 1000 ይከፍላል ፡፡
 13.  አሸናፊው በሁለት ቀናት ውስጥ ጥሬ ገንዘብ ካላስቀመጠ በዋስትና የተያዘው ሲፒኦ ወደ አምቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማህበር ይተላለፋል ፡፡
 14. ከባለቤትነት ማስተላለፍ ጋር የተያያዙ ሁሉም ክፍያዎች በአሸናፊው ይከፈላል።
 15. አምቦ ማዕድን ውሃ አ.ማ ተሽከርካሪው ከአምቦ ግቢ ከመውጣቱ በፊት ለማንኛውም የህግ እና ተያያዥ ጉዳዮች ኃላፊነቱን ይወስዳል ፡፡
 16. ከላይ ያሉትን ማናቸውንም መስፈርቶች አለመሟላት ከጨረታው ውድቅ ያስደርጋል ፡፡
 17. ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ብቻ በኩባንያው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይነገራቸዋል ወይም በስልክ ይገናኛሉ ወይም በአድራሻቸው ይነገራቸዋል ፡፡

መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃዎችን ከድርጅቱ ግዢ ክፍል በሚከተሉት ቁጥሮች ማግኘት ይችላሉ 0911825651 ወይም 0911939397/ በተጨማሪም ተሽከርካሪዎቹን ቃሊቲ በሚገኘው ድርጅታችን ግቢ በመገኘት መጎብኘት አንደሚችሉ አናሳውቃለን።

የአምቦ መዕድን ውሃ አክሲዮን ማህበር ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Send me an email when this category has been updated