አምቦ ማዕድን ዉሃ አክስዮን ማህበር በጨረታ አወዳድሮ መኪናዎችን መከራየት ይፈልጋል

Ambo-Mineral-Water-S.c.-Logo-2

Overview

  • Category : Vehicle Rent
  • Posted Date : 07/13/2021
  • Phone Number : 0911939397
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 07/30/2021

Description

የመኪና ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን አምቦ ማዕድን ዉሃ አክስዮን ማህበር በጨረታ አወዳድሮ መኪናዎችን መከራየት ይፈልጋል ማለትም ከከተማ ውጪ እና ለከተማ አገልግሎት የሚሰጡ ቀላል መኪናዎችን ፒክ አፕ፣ሲንግል ካብ ፣ ኪን ካብ፣ያለ ሹፌር  መከራየት ስለሚፈልግ ማከራየት የሚፈልግ ማንኛውም የዘመኑን ግብር የከፈለና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው  ለሚያከራየው መኪና ሙሉ ኢንሹራንስ ያለው ድርጅት ወይም ግለሰብ የቫት ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል የመኪናውን አይነት እና የስሪት ዘመኑን በመጥቀስ የሚያከራይበትን ዋጋ ከቫት በፊት በመግለፅ በሰም በታሸገ ፖስታ በማዘጋጀት የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የሚገኝበት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ቢሮ አንደኛ ፎቅ ግዢ ክፍል ከተፈረመበት የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማያያዝ መወዳደር የሚችል ሲሆን ጨረታውም ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በሰባት የስራ ቀናት ውስጥ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሐምሌ 23 2021 እአአ ከቀኑ 8 ሰዓት ሰዓት ይከፈታል ፡፡ የጨረታዉ አሸናፊ በሶስት የስራ ቀናት ዉስጥ ውል በመፈራረም ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-አክስዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0911939397/0924603406 መደወል ይቻላል

Send me an email when this category has been updated