አምደሁን ጠቅላላ ንግድ ኃ.የተ.የግል ማህበር አገልግሎት የሰጡ ተሽከርካሪዎች& የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች& የአልሙኒየም ቁርጥራጭ እና የተለያዩ ብረታ ብረቶች& አሮጌ ጐማ& ባትሪ& የተለያዩ አዲስ የመብራት ማብሪያ ማጥፊያ እና ካርቶን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Steels & Aluminium supply & sale
 • Posted Date : 04/24/2021
 • Phone Number : 0111266600
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/10/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

አምደሁን ጠቅላላ ንግድ ኃ.የተ.የግል ማህበር አገልግሎት የሰጡ ተሽከርካሪዎች& የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች& የአልሙኒየም ቁርጥራጭ እና የተለያዩ ብረታ ብረቶች& አሮጌ ጐማ& ባትሪ& የተለያዩ አዲስ    የመብራት ማብሪያ ማጥፊያ እና ካርቶን  ባሉበት ሁኔታ በዝግ  ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ/ቁ

የተሽከርካሪ ዓይነት

የተሰራበት

ዓመተ ምህረት

የሰሌዳ ቁጥር

ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ

1

ኒሳን ሰኒ  አውቶሞቢል

2003

3-25799 አአ

አምደሁን ጠቅላላ ን/ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለቡ ሪል እስቴት ጊቢ

ከሆኘ ዩኒቨርሲቲ ጀርባ

2

ዳይሐትሱ ቴሪዮስ

1998

3-A14026 አአ

           ”              “

3

ፊያት ገልባጭ 330-36

1994

3-37653 ኢት

           ”              “

4

ቶዮታ ፒክ ኒክ

1996

3-09562 አአ

           ”              “

5

ቶዮታ ሚኒ ቫን

1992

3-14962 አአ

           ”              “

6

በተጨማሪ፡-የማርብል ማምረቻ ማሽን& የሰሊጥ ማበጠሪያ& ያገለገሉ የከባድና ቀላል መኪና ጎማዎች በቁጥር& የአልሙኒም ቁርጥራጮች& የቀላልና ከባድ መኪናዎች ባትሪ& ያገለገሉ ፓኔሎችና መለዋወጫዎች& የኘላስቲክ ጄሪካኖች& አሮጌ ኮምፒዩተሮች& ኘሪንተሮች& የተሰራ የውሃ ታንከር እና ሌሎች

 1. ተጫራቾች የሚጫረቱትን ተሽከርካሪ (ንብረት) ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ዋና ቢሮ ፒያሳ ካንትሪ ታወር 7ኛ ፎቅ የኩባንያችን ዋና መስሪያ ቤት በመምጣት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች ንብረቶቹ የሚገኙበት አምደሁን ጠቅላላ ን/ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለቡ ሪል እስቴት እና ቃሊቲ ሣሙና ፋብሪካ ለጨረታ የገዙትን ሰነድ ይዞ በመሄድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማየት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በአምደሁን ጠቅላላ ንግድ ኃ/የተ/የግል ማህበር ስም የሚጫረቱት መኪና ዋጋ ብር 20,000 እና ለሌሎች ንብረቶች በጥቅል ብር 5,000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (C.P.O) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
 4. ተጫራቾች ሊገዙ የሚፈልጉትን ንብረት በሰም በታሸገ ፖስታ ከ 18/08/13 ዓ.ም. እስከ 02/09/13 ዓ.ም. ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ ዋናው መ/ቤት ፒያሳ ካንትሪ ታወር 6ኛ ፎቅ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ጨረታው በቀን 02/09/13 ዓ.ም. 11፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡
 6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለቡ በሚገኘው አምደሁን ሪል እስቴት ግቢ 03/09/13 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ካልተገኙ ጨረታው ታዛቢዎች ባሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
 7. የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የማስከፈያ ሰነድ ከዋናው መ/ቤት በመውሰድ ክፍያውን ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡
 8. የጨረታው አሸናፊዎች ክፍያ በፈፀሙ በ15 ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርትና ወጪ ንብረቱን ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
 9. የጨረታው አሸናፊዎች ክፍያ በተቀመጠው በ10 ቀናት የጊዜ ገደብ ካልከፈሉ ጨረታው ውድቅ ሆኖ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ አይደረግም፡፡
 10. በጨረታው ለተሸነፉ ያስያዙት C.P.O ወዲያው ይመለሳል፡፡ ለጨረታው አሸናፊዎች ያስያዙት ገንዘብ ለሚገዙት ንብረት ከሚከፍሉት ዋጋ ይታሰብላቸዋል፡፡
 11. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ንብረት የሚገዙበትን ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ በግልፅ በጨረታው ሰነድ ላይ ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
 12. ሁሉም ተሽከርካሪዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር /ሊብሬ/ ያላቸው ሲሆን በተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈለግ የስም ማዘዋወሪያ ወጪዎችን አሸናፊ ተጫራች ይከፍላል፡፡
 13. ሁሉም ተሽከርካሪዎች ቀረጥ የተከፈለባቸው ናቸው፡፡
 14. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

      ለተጨማሪ ማብራሪያ

      በስልክ ቁጥር 0111-26-66-00/01 ሞባይል 0910-42-87-10 ወይም ፒያሳ ካቴድራል ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ካንትሪ ታወር 7ኛ ፎቅ በመምጣት ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡