አሰር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር የኮንስትራክሽን ዕቃዎችና ማሽኖች የማጓጓዝ ስራ በቋሚነት የሚያመላልሱ የትራንስፖርት ማህበራት ወይም ባለንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለ2015 ዓ.ም ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Aser-Constraction-logo

Overview

 • Category : Transport Service
 • Posted Date : 09/11/2022
 • E-mail : info@aswrplc.com
 • Phone Number : 0116620357
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/16/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን አሰር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር በአዲስ አበባና ዙሪያዋ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ክልል ውጭ ወደ አሣይታ እና ሌሎች ክልል ከተማዎች የሚደረጉትን የኮንስትራክሽን ዕቃዎችና ማሽኖች የማጓጓዝ ስራ በቋሚነት የሚያመላልሱ የትራንስፖርት ማህበራት ወይም ባለንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለ2015 ዓ.ም ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የሚቀርቡ ሠነዶች

 1. የማህበሩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤
 2. በማህበሩ ስር ጭነቱን የሚያካሄድ ተሽከርካሪዎች ሊብሬ /ንግድ ፈቃድ፤
 3. ሙሉ ኢንሹራንስ 3ኛ ወገን የታደሰ እና የትራንስፖርት ኢንሹራንስ
 4. ቲን ሠርተፍኬት የማህበሩ፤

 

ተጨማሪ ነጥቦች

 1. ተወዳዳሪ ወይም ተጫራቾች ለሚደረገው ጭነት ትእዛዝ በአፋጣኝ ምላሽ መስጠት የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
 2. ዋጋ የሚሰጠው በተያያዘው ሰንጠረዥ መሆን አለበት፡፡
 3. ሌሎች ዝርዝር አሰራር ሂደቶች በውል ላይ የሚገለፁ ይሆናሉ፡፡
 4. በሀገራዊ ሁኔታ ለሚኖሩ የዋጋ ጭማሪዎች ድርጅቱ በተለየ መልኩ የዋጋ ማሻሻያ ያደርጋል፡፡
 5. ተጨማሪ ሳይቶች በሚኖሩበት ወቅት የጨረታው አሸናፊ በዚህ ጨረታ መነሻ ዋጋ መሠረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡
 6. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት /7/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውሰጥ ለጨረታው የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ በኩባንያው የመሣሪያዎች አስተዳደር መምሪያ ቢሮ በመቅረብ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ዶክመንቱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ በማሸግ መሣሪያዎች አስተዳደር ቢሮ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 7. ጨረታው መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የሚዘጋና ጨረታው በዚያው ቀን መስከረም 11/2015 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ9፡00 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
 8. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

P.O.Box: 5564

Addis Ababa, Ethiopia

Telephone: + 251 11 662 0357 / +251 940 285109

Facsimile:  + 251 11 618 9485

E-mail: info@aswrplc.com

aser@ethionet.et