አቢሲኒያ ባንክ አ.ማ የሰጠዉ ብድር ባለመከፈሉ በዕዳ ማካካሻነት የወረሰዉን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሻሻለዉ 216/92 መሠረት ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Abissiniya-Bank-1

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 10/03/2022
 • Phone Number : 0111264594
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/12/2022

Description

         የሃራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲኒያ ባንክ አ.ማ የሰጠዉ ብድር ባለመከፈሉ በዕዳ ማካካሻነት የወረሰዉን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሻሻለዉ 216/92 መሠረት ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የመኖሪያ ቤቶች እና መጋዘን

ተ.ቁ የተበዳሪዉ ሥም ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ የጨረታ መነሻ ዋጋ የንብረቱ ዓይነት የቦታው ጠቅላላ ስፋት በካ.ሜ ካርታ ቁጥር ጨረታ የወጣበት ጊዜ የጨረታዉ ሰነድ የሚገኝበትና የሚከፈልበት ቦታ እና ቀን
1 ዘነበ ተክሉ ሰንዳፋ 782,431.17 መኖሪያ ቤት 200ካ.ሜ 756/243/2002 የመጀመሪያ  

አ.አ ከሰሜን ሆቴል ጎን በሚገኘዉ አቢሲኒያ ባንክ ሕንፃ ሁለተኛ ፎቅ አስተዳደር እና ሎጂሰቲክስ መምሪያ

ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል

2 ወንድወሰን የኔሰዉ ሰንዳፋ 1,855,000.00 መጋዘን 500 ካ.ሜ 370/3101/97 የመጀመሪያ
3 ጂ.ዜድ.ኤ. ትሬዲንግ  ኃ/የግ/ማ አ/አ-ቃሊቲ 8,099,610.68 ያልተጠናቀቀ የመኖሪያ ቤት 427 ካ.ሜ 06097/4 የመጀመሪያ

የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች

ተ.ቁ የመለዋወጫዎቹ አይነት የመለዋወጫዎቹ መነሻ ዋጋ የመለዋወጫዎቹ የሚገኙበት ቦታ የጨረታዉ ሰነድ የሚገኝበትና የሚከፈልበት ቦታ እና ቀን
 

ለገጣፎ በሚገኘዉ የባንኩ መጋዘን መለዋወጫዎቹን

ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይቻላል፡፡

 

አ.አ ከሰሜን ሆቴል ጎን በሚገኘዉ አቢሲኒያ ባንክ ሕንፃ ሁለተኛ ፎቅ አስተዳደር እና ሎጂሰቲክስ መምሪያ

ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል

1 የአትላስ ኮፕኮ መለዋወጫዎች 241,857.02
2 የዳይናፓክ መለዋወጫዎች 433,501.31
3 የኤክስካቫተር መለዋወጫዎች 288,395.49
4 የቢኤም ደብሊዉ/BMW/ መለዋወጫዎች 1,101,365.74
ጠቅላላ ዋጋ 2,065,119.57

ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

 • ተጫራቾች የሚጨራቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋዉን ¼(አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በአቢሲኒያ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታዉ መሳተፍ ይችላል፡፡
 • ስለጨረታ አካሄድ እና ስለንብረቶቹ ዝርዝር መግለጫ የያዘዉን ሰነድ ሰሜን ሆቴል አጠገብ የሚገኘዉ የባንኩ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ አስተዳደር እና ሎጂሰቲክስ መምሪያ ወይም ንብረቶች በሚገኙበት የባንኩ ቅርንጫፍ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.(ብር እንድ መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መዉሰድ ይቻላል፡
 • ተጫራቾች ንብረቱን ለመግዛት የሚሰጡት ዋጋ ከጨረታ ሠነዱ ላይ በተያያዘዉ የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ካሰፈሩ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በመያዝ በሰም በታሸገ ፖስታ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም  ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ አዲስ አበባ አስተዳደር እና ሎጂሰቲክስ መምሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ አስመዝግበዉ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
 • የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን (አስራ አምስት) ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች/መረከብ ይኖርበታል፡፡ በነዚህ ቀናት ዉስጥ ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨረታዉ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታ ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
 • የጨረታዉ አሸናፊ ከሚገዙት ንብረት ጋር የተያያዘ ማንኛዉንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች እና ግብር የተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) እና ከስም ዝዉዉር ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን ገዢ ይከፍላል፡፡
 • ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዘዉ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል፡፡
 • በባንኩ የብድር ፖሊሲ መመሪያ መሠረት መስፈርቱን የሚያሟላ የጨረታዉ ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
 • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉን አ.አ ከሰሜን ሆቴል ወረድ ብሎ የባንኩ በላይ ዘለቀ ህንጻ 2ኛ ፎቅ አስተዳደር እና ሎጂሰቲክስ መምሪያ ወይም በአቅራቢያ ባሉ የባንኩ ቅርንጫፎች ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0111-26 45 94 እና 0918-77 84 27 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 • ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በማንናዉም ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

                                      አቢሲንያ ባንክ አ.ማ