አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 07/17/2022
- Phone Number : 0115150711
- Source : Reporter
- Closing Date : 08/13/2022
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ ግብር ፣ በተጠቀሱት ንብረቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችንም ገዢ ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪውን የወደፊት የሊዝ ክፍያ ገዢ ይከፍላል፡፡
- ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
- የጨረታው ቦታ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ላንቻ አካባቢ ህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ከነበረው ህንጻ ጎን ካለው አልፓውሎ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በባንኩ ህግ መምሪያ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-150711 እና 0115 54 67/37 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
t.q$ |
ytbĶW SM |
ከተበዳሪው የሚፈለግበት
ቀሪ ዕዳ |
የመያዣ ስጪው ስም |
የንብረቶቹ ዓይነትና አገልግሎት | የቦታው ስፋት በካ.ሜ | የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታ
መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ
ሰዓት |
ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
1 |
ስንታየሁ እና ወቴ የግንባታ ዕቃዎች አቅራቢ ማህበር |
እስከ ታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ብር672,993.08 |
ተበዳሪው |
መኖሪያ
ቤት |
140
|
M/D/K-367/2001 | በኦሮ/ብ/ክ/መ
ዱከም |
1,274,557.81
|
ነሐሴ 7 ቀን 2014 ዓ.ም | 4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |
ለሁለተኛ ጊዜ |