አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከተዉን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሸሻለዉ) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 01/14/2023
- Phone Number : 0115150711
- Source : Reporter
- Closing Date : 02/15/2023
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከተዉን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሸሻለዉ) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ ግብር ፣ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው መያዥ ንብረት ላይ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ ( ሻጩን ወክሎ) የሚከፍል ሲሆን ለቀሪ የሊዝ ክፍያ ገዢው ለሚመለከተው የመንግስት አካል ይከፍላል ፡፡
- ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ/አሸናፈ/ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
- የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት የነበረው ህንፃ ጎን ካለው አልፓውሎ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በባንኩ ህግ መምሪያ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-150711 እና 0115 54 67 37/36 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | ከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ ዕዳ | የመያዣ ሰጪው ስም | የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት | የቦታው ስፋት | የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር | ጨረታው የሚካሄድበት ቀን | የምዝገባ ሰዓት | የጨረታ ሰዓት | ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
1. | አቶ ተሾመ አንተነህ አለምነህ | እስከ ጥቅምት 09 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ብር 82,197,114.12 |
አቶ ተሾመ አንተነህ አለምነህ |
መኖሪያ ቤት |
136.00 ካ.ሜ
|
ኮ/ቀ/የማ/ን/መ/171/14922/01 |
አ/አበባ ከተማ ኮ/ቀራንዮ ክ/ከ ወረዳ 14 |
7,303,180.17 |
የካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም
|
4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |
የመጀመሪያ |
2. |
ሳሙኤል ገ/ማርያም |
እስከ ታህሳስ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ብር 14,692,305.88 |
ተበዳሪው |
72% (ሰባሁለት በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀ G+4የሆነ መኖሪያ ቤት | 163
ካ.ሜ |
ቦሌ 10/108/10/8/8054/109535/01 |
አ/አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 10 |
10,727,548.81 |
የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም
|
4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |
በድጋሚ |
3. | እነጉበና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር | እስከ ታህሳስ 02ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ብር 30,126,576.20 | ወ/ሮ ወርቅየ አበባ አባደፍር |
መኖሪያ ቤት |
1000 ካ.ሜ | L/X/L/D/6082/05 | በኦሮ/ብ/ክ/መ ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ቀበሌ 01 |
15,575,040.00 |
የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም
|
4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 | በድጋሚ |