አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 06/05/2021
- Phone Number : 0115150711
- Source : Reporter
- Closing Date : 07/22/2021
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ ግብር ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችንም ገዢ ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
- የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ጎን ካለው አልፓውሎ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በባንኩ ህግ መምሪያ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-150711 እና 0115 54 67 37/36 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
t.q$ |
ከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ ዕዳ |
የመያዣ ስጪው ስም |
የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት |
የቦታው ስፋት |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
1 |
እስከ ጥር 20 ቀን 2012 ብር 4,328,154.23 |
ተበዳሪው |
በግንባታ ላይ ያለ G+2+T መኖሪያ ቤት |
230 ካ.ሜ |
ቦሌ/ሊዝ/ጨ4/43/ 11/14/10654/00 |
በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 10 |
7,019,400.00 |
ሐምሌ 6 ቀን 2013ዓ.ም |
4:30-5:30 |
5፡30-6፡00 |
በድጋሚ |
2 |
እስከ ጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም ብር 7,638,182.27 |
ተበዳሪው |
G+2 እና G+1 መኖሪያ ቤት |
300 ካ.ሜ |
AA000090602133 |
አ.አ ኮ/ቀራንዮ ክ/ከተማ፣ወረዳ 06 |
8,180,860.78 |
ሐምሌ 8 ቀን 2013ዓ.ም |
4:30-5:30 |
5:30-6:00 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
3 |
እስከ ታህሳስ 03 ቀን 2012 ዓ.ም ብር 4,335,283.01 |
ተበዳሪው |
መጋዘን |
500 ካ.ሜ |
370/3101/97 |
በኦ/ብ/ክ/መንግስት ሰንዳፋ፣ከተማ ቀበሌ 01 |
1,855,000.00 |
ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም |
4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |
ለመጀመሪያ ጊዜ
|
4 |
እስከ እ.ኤ.አ እስከ 13/03/2019 ድረሰ ብር 2,125,393.47 |
ተበዳሪው |
G+2 መኖሪያ ቤት |
250 ካ.ሜ |
ግ/20/4/1159/2003 |
ባህር ዳር ቀበሌ 14 |
3,811,710.00 |
ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም |
4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |
ለሁለተኛ ጊዜ |