አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለ2015 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ የደንብ ልብሶችን በግልፅ ጨረታ ብቃት ያላቸው ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Abissiniya-Bank-4

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 08/20/2022
 • Phone Number : 0115584271
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/11/2022

Description

   የጨረታማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አባ/ግአ/ግ-05/2022

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለ2015 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ የደንብ ልብሶችን በግልፅ ጨረታ ብቃት ያላቸው ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የዕቃውአይነት መለኪያ ብዛት
1 ብትን ጨርቅ (ቴትሮን) 6000 በሁለት ከለር በሜትር 9,101
2 የሴቶች ጫማ በሁለት ከለር ጥንድ 2048
3 የወንዶች ጫማ በሁለት ከለር ጥንድ 1,227
4 የወንድ ሸሚዝ አራት ዓይነት ከለር በቁጥር 2,455
5 የሴት ሸሚዝ አራት ዓይነት ከለር በቁጥር 4,096
6 የሴት ካልሲ አራት ዓይነት ከለር በቁጥር 3,724
7 የወንድ ካልሲ አራት ዓይነት ከለር በቁጥር 2,455
8 ክራባት በሁለት ከለር በቁጥር 1,228
9 የፕላስቲክ ጓንት በጥንድ 334
10 የአፍ መሸፈኛ በቁጥር 1650
11 የጥበቃ ካርፓት በቁጥር 70
12 የዝናብ ልብስ ለሞተረኛ በቁጥር 7
13 ካኪ ኦቨርኮት በቁጥር 220

ጨረታው በባንኩ የግዥ መመሪያ የግልፅ ጨረታ ሂደትን ተከትሎ የሚፈፀም ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ  ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ ከገቢዎች ሚኒስቴር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ስታዲዮም ፊትለፊት በሚገኘው የሓ ሕንፃ ሰባተኛ ፎቅ ከባንካችን ግዥ አገልግሎት መምሪያ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 4. በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ብር በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ በተጫራቹ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እስከ መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ስታዲዮም ፊት ለፊት በሚገኘው የሓ ህንጻ ሰባተኛ ፎቅ በሚገኘው የባንካችን ግዥ አገልግሎት ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ከላይ በተጠቀሰው ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
 7. ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 8. ተጨማሪ ማብራሪያ በሚያስፈልግበት ጊዜ በግዥ አገልግሎት ስልክ ቁጥር 0115584271/0115504462 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ