አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለ2015 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ የስጦታ ቁሳቁሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Abissiniya-Bank-6

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 08/27/2022
 • Phone Number : 0115584271
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/12/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ግአ/ግ-11/2014

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለ2015 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ የስጦታ ቁሳቁሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ ዝርዝር መግለጫ መለኪያ ብዛት
1 ባለ ብዙ ጥቅም የእስክሪፕቶ ማስቀመጫ በቁጥር 1,000
2 እስክርቢቶ » 100,000
3 ቁልፍ መያዣ » 100,000
4 የደረት ጌጥ » 5,000
5 ኮፍያ » 13,000
6 ቲ-ሸርት ፖሎ » 5,000
7 ማግ » 5,000
8 የጠረጴዛ ሰታንድ (ኪው አር ኮድ) (Table standard/QR Code » 1,000
9 እቃ ለመያዣ የሚያገለግል ተንጠልጣይ ቦርሳ (Shopping Bag) » 10,000
10 ከወረቀት የሚሰራ የስጦታ ቦርሳ (Paper Gift Bag (IFB)) » 2,000
11 የወንድ ዣንጥላ » 7,500
12 የሴቶች ዣንጥላ » 4,500
13 የመኪና የፀሀይ መከላከያ » 7,000
14 የሴት ሰካርቭ » 5,000
15 ክራቫት » 5,000

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

 1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 2. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በአቢሲንያ ባንክ ሒሳብ ቁጥር ETB1502100010001 በመክፈል ከነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ስታዲዮም ፊት ለፊት በሚገኘው የሓ ሕንፃ ሰባተኛ ፎቅ ከባንካችን ግዥ አገልግሎት መምሪያ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
 4. በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 (መቶ ሺህ) ብር በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ በተጫራቹ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
 5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እስከ መስከረም 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ስታዲዮም ፊት ለፊት በሚገኘው የሓ ህንጻ ሰባተኛ ፎቅ በሚገኘው የባንካችን ግዥ አገልግሎት ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
 6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ከላይ በተጠቀሰው ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
 7. ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
 8. ተጨማሪ ማብራሪያ በሚያስፈልግበት ጊዜ በስልክ ቁጥር 0115584271/0115504462 መደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። E-mail BOAprocurement@bankofabyssinia.com.

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ