አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ በዋስትና የያዘውን ንብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 08/01/2021
- Closing Date : 08/16/2021
- Phone Number : 0115150711
- Source : Reporter
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ 15% ቫት እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎች ገዢ ይከፍላል፡፡ውዝፍ የሊዝ ዕዳ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ ዕዳ ወደ አሸናፊው /ገዢ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
- የጨረታው ቦታ አ.አ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ጎን ካለው አልፓውሎ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በባንኩ ህግ መምሪያ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-150711 እና 0115 54 67 37/36 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
t.q$ | የተበዳሪው ስም | ከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ ዕዳ | የመያዣው ሰጪው ስም | የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት | የቦታው ስፋት | የባለቤት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታ መነሻ ዋጋ | ጨረታው የሚካሄድበት ቀን | የምዝገባ ሰዓት | የጨረታ ሰዓት | ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
1 | አቶ ወንደሰን አንበሉ | እስከ የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ብር 2,317,410.00 | ተበዳሪው | መኖሪያ ቤት | 242.00ካ.ሜ | ቦሌ7/12/6/8/1/3805/3214/5739/02 | ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 | 5,889,148.16 | መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም | 4:30-5:30 | 5:30-6:00 | ለመጀመሪያ ጊ ጊዜ |
2 | ሀትና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር | እስከ ግንቦት 13 ቀን 2013ዓ.ም ድረስ ብር11,622,275.51 | ወ/ሮ ሳባ አጽብሃ | መኖሪያ ቤት | 250.00ካ.ሜ | ቦሌ9/74/4/5/ነ/301/504/01 | ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 09 | 8,435,000.00 | መስከረም 05 ቀን 2014 ዓ.ም | 4:30-5:30 | 5:30-6:00 | በድጋሚ |
3 | አቶ ሞላ ተመስገን | እስከ ሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብር15,400,000.00 | ተበዳሪው | G+2 መኖሪያ ቤት | 127.3ካሜ | AA0000907013827 | አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 7 | 6,410,193.40 | ነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም | 4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 | በድጋሚ |