አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ በእዳ ማካካሻት የወረሳቸውን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) 216/92 መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Abissiniya-Bank-5

Overview

  • Category : House & Building Foreclosure
  • Phone Number : 0583209660
  • Source : Reporter
  • Posted Date : 01/28/2023
  • Closing Date : 02/26/2023

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ በእዳ ማካካሻት የወረሳቸውን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) 216/92 መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ንብረቶች በሚገኙበት የባንኩ ቅርንጫፎ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መውሰድ ይቻላል፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ንብረቱን ለመግዛት የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፁ ካሰፈሩ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝ በስም በታሸገ ፖስታ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታው መካሄጃ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ በቅርንጫፎች ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስመዝግበው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋዜጣው በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ ግብር ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችንም ገዢ ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
  • ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
  • በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
  • የጨረታው ቦታ ንብረቶቹ በሚገኙበት ስፍራ ነው፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-9660 እና 058-320-6761 ባህር ዳር በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 

ተ.ቁ

የተበዳሪው ሙሉ ስም የመያዣ

ስጪው ስም

የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎትየቦታው ስፋትየባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የጨረታ

መነሻ ዋጋ

በብር

ጨረታው የወጣበት ጊዜ 

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

1ጂ.ዜድ.ኤ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበርተበዳሪውለኢንዱስትሪ የሚሆን ጅምር መካዘን8000 ካ.ሜ1307/2009አማራ ክልል ሞጣ ከተማ11,683,575.00ለመጀመሪያ ጊዜየካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም

ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት

 

 

2

 

አቶ  ዳዊት እሸቱ

 

ተበዳሪውለመኖሪያ150 ካ.ሜ11834/10 ቡሬ ከተማ ቀበሌ 03 715,680.00ለመጀመሪያ ጊዜየካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም   ከጠዋቱ 4፡00-6፡00
 አንተነህ ብርሃኔለመኖሪያ150 ካ.ሜ11735/10ቡሬ

ከተማ ቀበሌ 03

543,216.00ለመጀመሪያ ጊዜ የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም   ከሰዓት  8፡00-10፡30
 ፍስሃ ተስፋዬ መኖሪያ ቤት   150 ካ.ሜ11528/10ቡሬ

ከተማ ቀበሌ 03

411,731.25ለመጀመሪያ ጊዜ  የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00
4   ክንዱ አለበል

    ሽፈራው

ተበዳሪውመጋዘን   500 ካ.ሜክ-262-/2008አማራ ክልል ገንደውሃ ከተማ10,894,500.00ለመጀመሪያ ጊዜመጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00