አቢጃታ-ሻላ ሶዳ አሽ ያገለገሉ ቁሳቁሶችን፤ ለረጅም ጊዜ ያለ አገልግሎት የተቀመጡ ቱልሶችን እንዲሁም የመኪና አካላትን በእስክራፕ መልክ ሌሎችንም እንዴየእቃው ሁናቴ በገበያ ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Other Sale
  • Posted Date : 12/24/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/13/2023

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

አክሲዮን ማህበራችን አቢጃታ-ሻላ ሶዳ አሽ ያገለገሉ ቁሳቁሶችን፤ ለረጅም ጊዜ ያለ አገልግሎት የተቀመጡ ቱልሶችን እንዲሁም የመኪና አካላትን በእስክራፕ መልክ ሌሎችንም እንዴየእቃው ሁናቴ በገበያ ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ሥለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጫረታው መካፈል ትችላላችሁ፡-

1.ህጋዊ ፈቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ

2.የግብር ከፋይ (ቲን) ተመዝጋቢ የሆነ

3.የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ምዝገባ ፈቃድ ያላቸው

4.ተጫራቾች የተጠቀሰውን ዝርዝር በማየት ለእያንዳንዱ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል

5.ተጫራቾች በተሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ የጨረታ ዋጋ መስጠት አይቻልም

6.በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ አክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት ኤልፎራ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ላይ ንግድ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

7.ጨረታው ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3.00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3.30 ሰዓት ላይ የጨረታው ተሳታፊዎች በተገኙበት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8.አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

-ጨረታው በአክሲዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት በመምጣት ከታህሳስ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ታህሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም በመመልከት የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ከታህሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ጉርድ ሾላ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ኤልፎራ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በተጠቀሱት የጨረታ ማስገቢያ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 10.30 ገቢ በማድረግ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

-ጨረታው በአክሲዮን ማህበራችን ዋና መስሪያ ቤት ታህሳስ22 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ የውስጥ ኦዲት አገልግሎት እና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን፡-ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋቸውን መሠረት በማድረግ አክሲዮናችን ባስቀመጠው ዝርዝር መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ(cpo) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

-ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማንኛውንም ወጪዎች በሙሉ ገዢው ይሸፍናል፡፡

-የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪ ይከፍላሉ፡፡

-አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት የአክሲዮን ማህበሩ በስልክ ወይንም በቴሌግራም የሚያሳውቅ ሲሆን፤ውጤቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (ቀን) ቀናት ውስጥ አሻናፋዎች ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል፡፡

-አሸናፊዎች በምድብ የተቀመጡትን ዕቃዎች ቁሳቁሶችንና የመኪና አካላት በአዳሚ ቱሉ ጅዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ከዘዋይ 25 ኪ.ሜ በሚገኘው ከቡልቡላ ገባ ብሎ በሚገኘው ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወጪ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡

-ተጫራቾች  ለጨረታ የወጡትን ቁሳቁሶች በፋብሪካ ግቢ ውስጥ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር