አባከስ የሂሳብና የፋይናንስ አገልግሎት አክሲዮን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ

Overview

  • Category : Announcement
  • Posted Date : 10/15/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 10/29/2022

Description

የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

አባከስ የሂሳብና የፋይናንስ አገልግሎት አክሲዮን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በአያት አክሲዮን ማህበር ዋና ጽ/ቤት ሲሲኢ አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ  ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በስብሰባ ላይ እንዲገኙ የዳይሬክቶሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪ ያቀርባል፡፡

የጉባኤው አጀንዳዎች

1ኛ. የአክሲዮን ማህበሩ የስራ እንቅስቃሴ መገምገም እና የማህበሩን ቁመና መፈተሸ

2ኛ. የአክሲዮን ማህበሩ የስራ እንቅስቃሴ ከተገመገመ በኃላ ለማስቀጠል የማያስችል ሁኔታ ካለ ማህበሩ እንዲፈርስ በጠቅላላ ጉባኤ ማጸደቅ

በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች አግባብነት ባለው የመንግስት አካል የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን  ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ይዛችሁ በመቅረብ ጉባኤው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

በጉባኤው ላይ የምትገኙ  ባለአክሲዮኖች ኢትዮጲያዊነታችሁን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ  እንደዚሁም አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ ይዛችሁ የምትቀርቡ ተወካዮች የወካዮቻችሁን ኢትዮጲያዊነት የሚያሳይ  የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

በእለቱ ጉባኤው ተወያቶ የሚያሳልፈው ውሳኔዎች በጉባኤው ባልተገኙ አባላት ላይ ጭምር የጸና ይሆንል፡፡

አባከስ የሂሳብና ፋይናንስ አገልግሎት አ.ማ

የዳይሮክቶሮች ቦርድ