አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሠረት የውጭ አገር ዜግነት ከያዙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ባለአክስዮኖች ቀደም ሲል ከተረከባቸው ውስጥ ብር 1,246,350.00 ዋጋ ያላቸው 49,854 ተራፊ አክስዮኖችን ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት ኢትዮጵያዊ ለሆኑ ዜጎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Lion-International-bank-logo-1

Overview

  • Category : Share Foreclosure
  • Posted Date : 08/27/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 09/18/2022

Description

  የአክስዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሠረት የውጭ አገር ዜግነት ከያዙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ባለአክስዮኖች ቀደም ሲል ከተረከባቸው ውስጥ ብር 1,246,350.00 ዋጋ ያላቸው 49,854 ተራፊ አክስዮኖችን ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት ኢትዮጵያዊ ለሆኑ ዜጎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በማቅረብ መጫረት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፡-

  1. ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆኑ ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን አክስዮኖች መጠን ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ከባንኩ ዋና መ/ቤት የአክስዮን አስተዳደር ክፍል ወስደው በመሙላት፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚጫረቱበትን የአክስዮኖች ጥቅል ዋጋ ¼ኛ በባንኩ በተረጋገጠ ሲፒኦ እንዲሁም ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ኮፒ አያይዘው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሃያ ሁለት አካባቢ ‘ሌክስ ፕላዛ’ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ጨረታው መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም በባንኩ ዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  3. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ በማድረግ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ውጤቱ እንደታወቀ ለባንኩ ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች በግልም ሆነ በጋራ መጫረት ይችላሉ፡፡
  6. በሌሎች ሕጎችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ሕጎች ተፈፃሚነት አላቸው፡፡

                   ባንኩ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡