አንበሳ ጫማ አክስዮን ማህበርአንበሳ ጫማ አክስዮን ማህበር ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ስራዎች እና ግዢዎች ላይ ተጨራቾችን አወዳድሮ ማሰራት እና መግዘት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Paper Printed Advertising and Materials
  • Posted Date : 01/14/2023
  • Phone Number : 0114715454
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/27/2023

Description

አንበሳ ጫማ አክስዮን ማህበርአንበሳ ጫማ አክስዮን ማህበር ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ስራዎች እና ግዢዎች ላይ ተጨራቾችን አወዳድሮ  ማሰራት እና መግዘት ይፈልጋል፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የተቀመጡ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1.      21 የተለያዩ  መኪኖች (አውቶብሶች  ፤ ሚኒባሶች እና የጭነት መኪኖች) ላይ የሚሰራ የማስታወቂያ ፖስተር ብራንዲንግ ዲዛይን እና ስራ ፡፡

2.     የተለያየ ከለር ያላቸው ብዛት 2729   የሰራተኞች የደምብ ልብስ ቲሸርት  ግዢ

3.     የተለያየ ሳይዝ እና ከለር ያላቸው ቱታዎች  ከነ ሸሚዙ ፤ የተለያየ ከለር ያላቸው ጋዋን የደምብ ልብስ ፤የተለያየ ከለር ያላቸው ሱሪ እና ሸሚዝ ፤ የጥበቃዎች ኮፍያ  አጠቃላይ  የስራዎች ድምር 514 የደምብ ልብስ  ስፌት ስራ የስፌት የእጅ ዋጋ ብቻ (ልብስ ከድርጅታችን የሚቀርብ)፡፡

ü  የመኪና ብራንዲንግ ስራ ተጫራቾች የሚሰሯቸውን የዲዛይን እና ህትመት ዋጋ መለጠፊያ ጨምሮ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ü  በጨረታ ያሸነፈው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ከድርጅቱ ጋር ውል በመዋዋል ስራዉን መጀመር ይኖርበታል፡፡

ü  ተጨራቾች በሙያው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የወቅቱን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡

ü  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 100 በመክፈል ከፋይናንስ ክፍል መዉሰድ የሚችሉ ሲሆን እንዲሁም ጨረታዉ ፀንቶ የሚቆየዉ ጨረታዉ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ7ኛዉ ቀን ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአንበሳ ጫማ አ.ማ አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 02 መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ü  ተጫራቾች በተራ ቁጥር 3 ለተጠቀሰው የእጅ ስፌት ስራ ለመጫረት የሚያቀርቡትን ዋጋ 1%  (bill bond) እንዲሁም በጨረታው አሸናፊ ሲሆኑ የሚያቀርቡትን ዋጋ  (50%) performance bond ከታወቀ ባንክ በሲፕኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ü  ተጨራቾች ከላይ በተራ ቁጥር 1 ለተጠቀሰው የመኪና ብራንዲንግ ስራ ለመጫረት የሚያቀርቡትን ዋጋ 1%  (bill bond) እንዲሁም በጨረታው አሸናፊ ሲሆኑ የሚያቀርቡትን ዋጋ  (10%) performance bond ከታወቀ ባንክ በሲፕኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ü  ተጫራቾች በተራ ቁጥር 2 ለተጠቀሰው የደምብ ልብስ ግዢ ስራ ለመጫረት የሚያቀርቡትን ዋጋ 1%  (bill bond) እንዲሁም በጨረታው አሸናፊ ሲሆኑ የሚያቀርቡትን ዋጋ  (10%) performance bond ከታወቀ ባንክ በሲፕኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ü  ተጨራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከታች በተገለጸው አድራሻ በተዘጋጀው ሳጥን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

አድራሻ- አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 2 ቆርቆሮ ፋብሪካ ገባ ብሎ ካለው ዋና ፋብሪካ  ፋይናንስ  ቢሮ

ለበለጠ መረጃ ፡-..0114715454/0114716956