አካካስ ሎጅስቲክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እያገለገሉ ያሉ የጭነት ተሽከርካሪዎች፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Vehicle Sale
  • Posted Date : 11/06/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/15/2022

Description

ማሳሰቢያ እያገለገሎ ያሉ የጭነት ተሸከረካሪዎች ሽያጭ

አካካስ ሎጅስቲክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እያገለገሉ ያሉ የጭነት ተሽከርካሪዎች፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  • ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን የተሽከርካሪዎችን የጨረታ ሰነዱን ወሎ ሰፈር ተባበር በረታ ህንፃ 4ኛ ፎቅ በፋይናንስ መምሪያ ገንዘብ ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታውን ጠቅላላ ዋጋ 20% የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅቱ ስም በማሰራት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡በጨረታው ለተሸነፉ ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል፡፡ አሸናፊዎች በጨረታው ላሸነፉት ንብረት ቀሪውን ክፍያ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
  • ጨረታው የሚዘጋበት ቀን ህዳር 06 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን ፣ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዕለቱ ህዳር 06 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአካካስ ሎጅስቲክስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
  • የተሸከረካሪዎችን አጠቃላይ ሁኔታ በግንባር ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ቃሊት ጉምሩክ ፊት ለፊት በሚገኘው ጊፊት ፉድ ኤንድ ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር  ግቢ ውስጥ በስራ ሰዓት ማየት ይችላል፡፡
  • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አካካስ ሎጅስቲክስ ኃ/የተ/የግል ማህበር