አዋሽ ባንክ ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ የተገለፁትን ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለ በተሰጠው ስልጣንና ውክልና መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 10/15/2022
- Phone Number : 0115570075
- Source : Reporter
- Closing Date : 11/17/2022
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
አዋሽ ባንክ ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ የተገለፁትን ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለ በተሰጠው ስልጣንና ውክልና መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡
ተ.ቁ. | የተበዳሪው ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የንብረት አስያዥ ስም | የቦታ አገልግሎት | ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ | የካርታ ቁጥር | የቦታ ስፋት በካ.ሜ | የጨረታ መነሻ ዋጋ | የጨረታ ቀን | የጨረታ ሰዓት | ||
ከተማ | ክፍለ ከተማ | ቀበሌ /ወረዳ | ||||||||||
1 | ሲሳይ አዱኛ | ድሬዳዋ | ተበዳሪው | G+2 ለመኖሪያ ቤት | ገላን | – | – | BMG/18-330/2011 | 140 | 4,300,000 | 7-3-15 | 5፡00-6፡00 |
2 | ቤንች ማጂ አንድነት የገበሬዎች ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበር | ሚዛን ተፈሪ | ተበዳሪው | ለኢንደስትሪ | ሚዛን አማን | – | – | አጠ/20/261 | 8,000 | 9,300,000 | 7-3-15 | 5፡00-6፡00 |
3 | ገዙ ገቢሳ | አሰላ | ጋሻው አበበ | ለቅይጥ አገልግሎት | አዳማ | – | 72164/96 | 228 | 8,100,000 | 8-3-15 | 4፡00-5፡00 | |
4 | በዳዳ ዳዲ | ቦቴ | ተበዳሪው | የመኖሪያ ቤት | ቦቴ | – | – | WMM/MB/3879/07 | 200 | 600,000 | 8-3-15 | 8፡00-9፡00 |
5 | ግርማ ጅሎ | ያቤሎ | አባቱ ግርማ | የመኖርያ ቤት | ፊንጫዋ | – | – | BMF26/3138/06 | 400 | 425,000 | 8-3-15 | 4፡00-5፡00 |
6 | አብርሃም ጅሎ | ያቤሎ | ተበዳሪው | የመኖርያ ቤት | ፊንጫዋ | – | – | 26/26/07 | 200 | 270,000 | 8-3-15 | 5፡00-6፡00 |
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ባለዕዳው ወይም ሕጋዊ ወኪሉ፣ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት የባንኩ ዋናው መ/ቤት ጊዜያዊ ጽ/ቤት በሚገኝበት ህንጻ በሚገኘው የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር ቢሮ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ከተራ ቁጥር 2-6 የተዘረዘሩት ንብረቶች ጨረታ ደግሞ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ባለዕዳዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ንብረቶቹ በሚገኙበት ግቢ ውስጥ ይካሄዳል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ግን ባንኩ ዋጋውን የሚቀበል መሆን አለመሆኑን ጨረታው ከተደረገበት ቀን ቀጥሎ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ለተጫራቹ ያሳውቃል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች የአሸናፊነት ደብዳቤ ከባንኩ ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርግ ተጫራች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ከመኖሪያ ቤቶች ውጭ ባሉ ንብረቶች ሽያጭ ላይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ የሚታሰብ ሲሆን ሁሉንም ንብረቶች በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያ ገዢ ይከፍላል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ፡፡- ድሬዳዋ ቅርንጫፍ 0251-11 42 51፣ሚዛን ተፈሪ ቅርንጫፍ 047-1-35-18-79፣አሰላ ቅርንጫፍ 0223-31 27 70 ፣ ቦቴ ቅርንጫፍ 022-1-15-04-92 ያቤሎ ቅርንጫፍ 0464-46 01 97 ወይም የሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 0115-57-00-75 ብሎ መደወል ወይም በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አዋሽ ባንክ