አዋሽ ባንክ አ.ማ ለሳይገን ዲማ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ያበደረው የሸቀጣ ሸቀጥ ብድር (Merchandise Loan) ባለመክፈሉ በዋስትና የያዛቸውን ፖሊስተር እና ሱፍ ብትን ጨርቆችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Awash-Bank-logo-Reportertenders-5

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 02/19/2022
 • Phone Number : 0115303102
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/08/2022

Description

 የጨረታ ማስታወቂያ

አዋሽ ባንክ አ.ማ ለሳይገን ዲማ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ያበደረው የሸቀጣ ሸቀጥ ብድር (Merchandise Loan) ባለመክፈሉ በዋስትና የያዛቸውን ፖሊስተር እና ሱፍ ብትን ጨርቆችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡   በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በመስኩ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡   ነገር ግን ለሠራተኛ ወይም ለትምህርት ቤት ደንብ ልብስ የሚፈልጉ ከሆነ ከድርጅታቸው ደብዳቤ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

 • ስለ ጨረታው አፈጻጸም የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሳ/ በመክፈል በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዋሽ ባንክ አ.ማ. ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ የሕንጻና የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 1-08 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 28 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 10 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ልደታ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ህንፃ ምድር ቤት የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመያዝ ጨርቆቹን ማየት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች ሁለቱንም ዓይነት ጨርቆች የሚገዙበትን የመነሻ ዋጋ ¼ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ(CPO) በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አክስዮን ማህበር ስም አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ያለ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 • ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን የጨረታ ሰነዶች በታሸገ ፖሰታ (ኤንቨሎፕ) እስከ የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ልደታ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ባልቻ ሳፎ ህንጻ የሕንጻና የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 1-08 ይከፈታል።
 • እያንዳንዱ ተጫራች ለሚጫረትበት የጨርቅ ዓይነት በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ለይቶ በመጻፍ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡   ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሠዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0115-303102/04 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አዋሽ ባንክ አ.ማ.