አዋሽ ባንክ አ.ማ. በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ከልደታ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ ለካፌ እና ሬስቶራንት የሚሆን ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : House & Building Rent
  • Posted Date : 09/24/2021
  • Phone Number : 0115303102
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 10/12/2021

Description

አዋሽ ባንክ አ.ማ. በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ከልደታ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ ለካፌ እና ሬስቶራንት የሚሆን ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በሚሰሩበት የሥራ መስክ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡  ስለጨረታው አፈጻጸም የተዘጋጀውን የሚከራይ ክፍል ሁኔታ በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ብር 100.00/አንድ መቶ/ ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ይዞ አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 9ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 9-04 በማቅረብ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ መውሰድና ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ክፍሉን መጐብኘት ይቻላል፡፡

ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ሰነዶች በታሸገ ፖስታ/ኤንቨሎፕ/ እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፣ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

እያንዳንዱ ተጫራች የኪራይ ጨረታ መነሻ ዋጋ የ3 ወር ¼ኛውን በአዋሽ ባንክ አ.ማ. ስም ሲፒኦ(CPO) በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

ያለ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

ጨረታው ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ልደታ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 9ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 9-04 ውስጥ ይከፈታል፡

ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0115-303102/04 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር