አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2፣ ሸዋ ሱፐር ማርኬት አጠገብ በአቢሲኒያ ሪል እስቴት ሕንፃ ምድር ወለል የሚገኘውን በጠቅላላው 113.6 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቢሮ በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል

AWASH-BANK-logo-1

Overview

 • Category : House & Building Rent
 • Posted Date : 03/20/2021
 • Phone Number : 0115570001
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/01/2021

Description

መጋቢት 8 ቀን 2013 ዓ.ም

የቢሮ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2፣ ሸዋ ሱፐር ማርኬት አጠገብ በአቢሲኒያ ሪል እስቴት ሕንፃ ምድር ወለል የሚገኘውን በጠቅላላው 113.6 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቢሮ በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት ማሟላት አለባችሁ፡፡

 • ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃና ለጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸውና የግብር ሰብሳቢ ባለሥልጣን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት 4ፎቅ የግዢ፣ሎጀስቲክስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ተመስርተው ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 (ሁለት በመቶ) በሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ (Bid Bond) በማሠራት በኩባንያው ዋና መ/ቤት 4ፎቅ ግዢ፣ሎጀስቲክስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች የሚሠጡት ዋጋ ለካሬ ሜትር ወይም ቁርጥ ዋጋ መሆን አለመሆኑን ለይቶ ማቅረብ ሲኖርባቸው ይኸውም ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን እንደሚጨምር ማሳየት አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች የቅድመ ክፍያ ወይም አድቫንስ የምን ያህል ጊዜ መክፈል እንደሚችሉ መግለጽ አለባቸው፡፡
 • ጨረታው መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት 15ፎቅ በማኔጅመንት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

 

ማሳሰቢያ፡-   ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊልም የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-557-00-01 / 011-557-02-26/ የውስጥ መስመር 172፣272 እና 236 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡

አድራሻ፡ ከብሔራዊ ትያትር በስተጀርባ አዋሽ ታወርስ ሕንፃ ላይ

አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

Send me an email when this category has been updated