አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈፅሞባቸው ከደንበኞቹ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች እና ኩባንያው ሲገለገልባቸው የነበሩ ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ቁሳቁሶችንና ሌሎችንም ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Vehicle Sale
- Posted Date : 02/11/2023
- Closing Date : 03/02/2023
- Phone Number : 0115570001
- Source : Reporter
Description
አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈፅሞባቸው ከደንበኞቹ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች እና ኩባንያው ሲገለገልባቸው የነበሩ ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ቁሳቁሶችንና ሌሎችንም ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- በመሆኑም እነዚህን ዕቃዎች ለመግዛት የምትፈልጉ ሁሉ የተጐዱ ተሽከርካሪዎች ማቆያ ቃሊቲ ከሸገር ዳቦ ጎንና ቃሊቲ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ወይም ህብረት ኢንሹራንስ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆያ ጀርባ የኩባንያችን ሪከቨሪ በመገኘትና በማየት የምትገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ የካቲት 08 ቀን 2015 ዓ.ም. እስከ የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብሔራዊ ትያትር ጀርባ በሚገኘው አዋሽ ታወርስ የኩባንያው ዋና መ/ቤት አንደኛ ፎቅ ድረስ በመቅረብ የጨረታ መቅረቢያ ቅጽ በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው መጋቢት 02 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ቃሊቲ ከሸገር ዳቦ ጎን በሚገኘው የኩባንያችን ሪከቨሪ ይከፈታል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የመነሻ ዋጋቸው እስከ 5,000 ለሆኑት ብር 500፣ ከብር 5,001 እስከ ብር 10,000 ለሆኑት ብር 2,000 ከብር 10,001 እስከ 50,000 ለሆኑት ብር 5,000 ፣ ከብር 50,000 በላይ ለሆኑት የመነሻ ዋጋውን 10% /አስር በመቶ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ሁሉም የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ (CPO) መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ከተዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ ውጪ ሞልተው የሚያቀርቡት ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ከጨረታው በኋላ ያሉትን ወጪዎች በሙሉ ገዢው ይሸፍናል፡፡
- አሸናፊዎች ንብረቶቹን ጨረታው ከተካሄደበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ክፍያውን ፈጽመው ካልተረከቡ ጨረታው የሚሰረዝ ከመሆኑም በላይ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ አይደረግም፣ በሌላ በኩል ክፍያ ፈፅመው ዕቃዎቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ቢሆን ኩባንያው ኃላፊነት የለበትም፡፡
- በአዋጅጀ ቁጥር 681/2010 አንቀፅ 6 (3) በተደነገገው መሠረት በጥገና ለሚከናወንባቸው ተሽከርካሪዎች የተሽከርካሪው የባለቤትነት ስም እንዲዛወርለት በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ለሚመለከተው የመንግስት መስሪያ ቤት ማመልከት ይኖርበታል፡፡
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.
ዋና መ/ቤት ‘ C 011 557 00 01 ፋክስ 7 C 011 557 02 08
የሪከቨሪ ‘ C 011 439 11 01 7 C 011 557 02 18
* C 12637 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ