አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ቅርንጫፍ ባንኮቹ በሚገኙበት ከተሞች የተለያዩ ቃሚ ንብረቶችን ለማጓጓዝ ይረዳው ዘንድ ማውረጃና መጫኛ ክሬን ያለው የጭነት መኪና ላልተወሰነ ጊዜ መከራየት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Vehicle Rent
- Posted Date : 10/26/2022
- Phone Number : 0115571107
- Source : Reporter
- Closing Date : 11/09/2022
Description
አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ
የጨረታ ማስታወቂያ
ማውረጃና መጫኛ ክሬን ያለው የጭነት መኪና ኪራይ
የጨረታ ቁጥር AB026/2022/23
- አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ቅርንጫፍ ባንኮቹ በሚገኙበት ከተሞች የተለያዩ ቃሚ ንብረቶችን ለማጓጓዝ ይረዳው ዘንድ ማውረጃና መጫኛ ክሬን ያለው የጭነት መኪና ላልተወሰነ ጊዜ መከራየት ይፈልጋል፡፡
- በመሆኑም ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው የጭነት መኪና የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ሶስት (3) ቶን እና ከዛ በላይ የማንሳት አቅም ያለው፡፡
- የቡሙ ርዝመት 9 ሜትር እና ከዛ በላይ የሆነ
- ከኃላ መሸከሚያ ካርጎ 70 ኩንታል የመጫን አቅም ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡
- በጨረታው የሚሳተፉ ድርጅቶች (ግለሰቦች) የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የሚጠበቅባቸውን የመንግስት ግብር ከፍለው ያጠናቀቁ የማከራየት ፍቃድ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
- በተጫራቾች የሚቀርበው ዋጋ በደንብ ሊነበብ በሚችል እጅ ፅሁፍ ወይም በኮምፒዩተር ተፅፎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለው ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
- በተጫራቾች የሚቀርበው ዋጋ ሹፌር እና የክሬን ባለሙያ ዋጋን ያካተተ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ የሹፌሩ መንጃ ፍቃድ ኮፒ አብሪ መቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የአንድ ወር ኪራይ ዋጋ በታሸገ ፖስታ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ኮሜርስ ጀርባ መዚድ ህንፃ ጎን በሚገኘው አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ጊዜያዊ ዋና መ/ቤት በሚገኝበት 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ግዢ ዋና ክፍል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተጫራቸች የቀረበው ዋጋ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት በአዋሽ እንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ግዢና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 ያሉትን መስፈርት ያላሟሉ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይሆናሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-57-11-07 ወይም 0115-57-00-84 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይንም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡