አያት አክሲዮን ማህበር ለቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ ማሽነሪዎች እና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን ጥገና ሥራ በቋሚነት ማከናወን የሚችሉና ይህንን አገልግሎት ለመስጠት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በጨረታ አወዳደሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

Ayat-Real-Estate-logo-reportertenders

Overview

 • Category : Machinery
 • Posted Date : 01/25/2023
 • Phone Number : 0907371588
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 02/07/2023

Description

አያት አክሲዮን ማህበር 

ለቀላል እና ከባድ ተሸከርካሪዎች፣ ማሽነሪዎች እና ለኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ጥገና  አገልግሎት የወጣ

የጨረታ ማስታወቂያ

 1. አያት አክሲዮን ማህበር ለቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ ማሽነሪዎች እና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን ጥገና ሥራ በቋሚነት ማከናወን የሚችሉና ይህንን አገልግሎት ለመስጠት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በጨረታ አወዳደሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከአክሲዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት ከመገናኛ ወደ ወሰን ግሮሰሪ በሚወስደው መንግድ ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል ጀርባ አያት አፓርትመንት ሞል ግንባታ አጠገብ በሚገኘው ቢሮ ጀርባ ሁለተኛ ፎቅ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ (ሽያጭ፤ ግዢና ንብረት አስተዳደር ዘርፍ) ቢሮ ቁጥር 214፤ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች በጨረታ ሠነዱ ላይ የተጠቀሱትን የቴክኒካል ፣ ፋይናንሻል እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሠነዶችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 4. ከላይ በተ.ቁ 3 ላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የምዝገባ ወረቀት እና የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 5. የጥገና አገልግሎት ሥራው የሚከናወነው በአያት አክሲዮን ማህበር ግቢ ውስጥ ሲሆን ተጫራቾች የሥራውን ይዘት ለመገንዘብ ይረዳቸው ዘንድ የቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ ማሽነሪዎች እና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን ወቅታዊ ይዘት ጨረታ ሠነዶቻቸውን ከማስገባታቸው በፊት በአካል ተገኝተው መመልከት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 6. የጥገና አገልግሎቱ   የሚከተሉትን ሥራዎች የሚያካትት ይሆናል፡፡
  • Engine Service
  • Break System Service
  • Power train (Power Transmission) System Service
  • Suspension System Service
  • Electrical System Service
  • Steering System Service
  • Body Repair, Painting, and welding Works
  • Hydraulic system Service
  • Other mandatory Services
 7. ጨረታው በአያት አክሲዮን ማህበር የጨረታ መመሪያ መሠረት የሚከናውን ሲሆን ህጋዊ ለሆኑና የሚፈለገውን አገልግሎት ለመስጠት ለሚችሉ ድርጅቶች ክፍት ነው፡፡
 8. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመሣተፍ በትንሹ  ለተመሣሣይ የስራ አይነት እና መጠን የ5 (አምስት ) አመታት ልምድ ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን ለዚሁም ተገቢውን ማስረጃ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ይሆናል፡፡
 9. ተጫራቾች የቴክኒካል፣ ፋይናንሻል እና የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና ሰነዶችን በሦስት የተለያዩ ኢንቨሎፕ በሰም አሽገው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ጨረታው የሚገባበት ቀን ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡
 10. ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 29 ቀን 2015 ዓም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ከጨረታ ማስገቢያው ሰዓት በኃላ የሚቀርብ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም ፡፡
 11. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለ 90 ቀናት የሚቆይ ብር 50,000 (አምሳ ሺህ) ብር በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና መሆን ይኖርበታል፡፡
 12. ማህበሩ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብት አለው፡፡

አድራሻ፤ አያት አክሲዮን ማህበር ዋናው መስሪያ ቤት፤

ከመገናኛ ወደ ወሰን ግሮሰሪ በሚወስደው መንግድ፤

 ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል ጀርባ

ለበለጠ መረጃ የስ.ቁ 0907371588 ወይንም 0908355240 ይደውሉ፡፡