አዲስ የብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ የወሰዱትን ብድር ባለመክፈላቸው ተቋሙ በአዋጅ ቁጥር 626/2001 እና በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ከዚህ በታች የተመለከቱትና በመያዣነት ወይም በዋስትናነት የተያዙ ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 12/24/2022
- Source : Reporter
- Closing Date : 01/14/2023
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘረው ተበዳሪዎች ከአዲስ የብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ የወሰዱትን ብድር ባለመክፈላቸው ተቋሙ በአዋጅ ቁጥር 626/2001 እና በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ከዚህ በታች የተመለከቱትና በመያዣነት ወይም በዋስትናነት የተያዙ ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተ/ቁ | የተበዳሪ ስም | የዋስ ስም | ቅርንጫፍ | የሰሌዳ ቁጥር | የመኪናው ዓይነት | መነሻ ዋጋ (ብር) | ሐራጅ የሚካሄድበት | ምርመራ | |
ቀን | ሰዓት | ||||||||
1 | በለጠ ደጀኔ | ጌታሁን አሰፋ | አራዳ ቅ.10 | 01-27601 አ.አ | ፔጆ | 60,000 | 04/5/2015 | ከጠዋቱ 4:00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
2 | ሲሳይ አፈወርቅ | ሲሳይ አፈወርቅ | አራዳ/ዲ | 02-34604 አ.አ | 4K DX | 40,000 | 04/5/2015 | ከጠዋቱ 4:00 | በድርድር |
3 | መዓዛ እንድሪስ | መዓዛ እንድሪስ | ቃሊቲ/ዲ | 03-40157 ኢት | IVECO Power | 200,000 | 04/5/2015 | ከጠዋቱ 4:00 | በድርድር |
4 | ናቃቸዉ ኖራሁን | ናቃቸዉ ኖራሁን | እፎይታ/ዲ | 02-91070 አ.አ | ፔጆ | 100,000 | 04/5/2015 | ከጠዋቱ 4:00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
5 | ዳዊት እሸቱ | ዳዊት እሸቱ | ሽሮሜዳ/ዲ | 03-A90192 አ.አ | ሊፋን 520 | 500,000 | 04/5/2015 | ከጠዋቱ 4:00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
6 | ራሄል ዮሀንስ | ናትናኤል ታሪኩ | አ/ቃ.ቃ.06 | 03-10841 አ.አ | ቶዮታ ፒክ አፕ | 400,000 | 04/5/2015 | ከጠዋቱ 4:00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
7 | ሱልጣን፤ ነኢማ፤ አብድላዚዝ እና ጓደኞቻቸዉ | ሱልጣን ሸሪፍ | ን/ስ/ላ ቅ.4 | 02-14148 አ.አ | DX | 300,000 | 04/5/2015 | ከጠዋቱ 4;00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
ማሳሰቢያ፡-
- ማንኛውም ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሉ የመኪናውን ሐራጅ መነሻ ዋጋ ¼ኛውን (አንድ አራተኛውን) በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡
- አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ ጨረታዉን ማሸነፉ በማስታወቂያ ሠሌዳ ከተለጠፈበት ቀን አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ካልከፈሉ ለሐራጅ መነሻ ያስያዘው ገንዘብ ተመላሽ አይደረግለትም፡፡
- ሐራጅ የሚካሄደው ቸርችል ጎዳና ሕብረት ኢንሹራንስ ሕንፃ አጠገብ በሚገኘው በተቋሙ ዋናው መ/ቤት ሕንፃ 7ኛ ፎቅ የሚገኘዉ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
- ተራ ቁጥር 2, 5 እና 7 ላይ የተጠቀሱትን የተሸከርካሪዎች ሁኔታ ለማየት ተሸከርካሪዎቹ በሚገኙበት ቦታ ቸርችል ጎዳና ሕብረት ኢንሹራንስ ሕንፃ አጠገብ በሚገኘው በተቋሙ ዋናው መ/ቤት ሕንፃ ግቢ ውስጥ ከጨረታዉ ቀን ቀደም ብሎ ባሉት ቀናት ረቡዕና አርብ በሥራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይቻላል፡፡
- ከተራ ቁጥር 1, 3, 4 እና 6 የተጠቀሱትን የተሸከርካሪዎች ሁኔታ ለማየት ተቋሙን ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል፡፡
- ተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰዉ ተሽከርካሪ እስከ 02/01/2015 ዓ.ም ድረስ ብር 24,465.94 /ሀያ አራት ሺ አራት መቶ ስልሳ አምስት ብር ከ94/100/ ከመንግሥት የሚፈለግ ግብር አለበት፡፡
- ተራ ቁጥር 3 ላይ የተጠቀሰዉ ተሽከርካሪ እስከ 12/12/2013 ዓ.ም ድረስ ብር 100,152.90 /አንድ መቶ ሺ አንድ መቶ ሀምሳ ሁለት ብር ከ90/100/ ከመንግሥት የሚፈለግ ግብር አለበት፡፡
- ተራ ቁጥር 5 ላይ የተጠቀሰዉ ተሽከርካሪ እስከ 04/13/2014 ዓ.ም ድረስ ብር 66,141.97 /ስልሳ ስድስት ሺ አንድ መቶ አርባ አንድ ብር ከ97/100/ ከመንግሥት የሚፈለግ ግብር አለበት፡፡
- ከተሸከርካሪዎቹ ከመንግሥት የሚፈለጉ ግብሮችን፣ የቦሎ ክፍያ፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን የጨረታው አሸናፊ ይሸፍናል፡፡
- በጨረታዉ ቀን የንብረቱ ባለቤት ወይም ሕጋዊ ወኪሉ በመገኝት ጨረታዉን መከታተል ይችላሉ ባይገኙም ጨረታዉ ይካሄዳል፡፡
- ተቋሙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 011-1-262233 ወይም 011-1-263447 በመደወል ወይም በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ሕግ ክፍል በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ