አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 626/2001 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Aggar-Micro-Finance-logo

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 09/24/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/05/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን  ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 626/2001 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

 

ተ.ቁ

 

የተበዳሪ/ዋ ስም

 

የንብረትአስያዥስም

 

የተበደሩበትቅርንጫፍ

 

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

 

የንብረቱ

መገለጫ

የጨረታው

መነሻዋጋ

ብር

ሐራጁ የሚካሄድበት
ቀን ሰዓት
1  ዘውዴተስፋ ልደት አልዓዛር ታረቀኝ ኮልፌ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረድ ብሎ ጎጆ ሆቴል ጀርባ በሚገኘው የኩባንያው በዕዳ የሚያዙ ተሸከርካሪዎች ማቆያ ጊቢ ውስጥ ሠ.ቁ ኢ.ት 03-29639

የተሰራበት ዘመን 1999

ጎታች ቱርቦ ስታር

500,000.00 መስከረም 24/2015 3፡00

4፡30

2 መሰረት ስለሺ መሰረት ስለሺ ቂርቆስ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረድ ብሎ ጎጆ ሆቴል ጀርባ በሚገኘው የኩባንያው በዕዳ የሚያዙ ተሸከርካሪዎች ማቆያ ጊቢ ውስጥ ሠ.ቁ አአ 03-76521 የተሰራበት ዘመን 2010 ዓ.ም ክሬን ፍቶን 229,262.00 መስከረም 24/2015 4፡30-6፡00
3 አቶ ዋሲሁን ደስታ አቶ አፈወርቅ ካሳዬ ቂርቆስ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረድ ብሎ ጎጆ ሆቴል ጀርባ በሚገኘው የኩባንያው በዕዳ የሚያዙ ተሸከርካሪዎች ማቆያ ጊቢ ውስጥ ሠ.ቁ አአ 02-81635

የተሰራበት ዘመን 1987 ዓ.ም መርቼዲስ አውቶ ሞቢል

78,000.00 መስከረም 24/2015 7፡00 -8፡00
4  ወ/ሮ አጸደ ተስፋዬ ወ/ሮ አጸደ ተስፋዬ ዱከም ዱከም ከተማ ቀበሌ 01 ሠ.ቁ፡-አአ-03-A56995

የተሰራበት ዘመን 2006 ጀርመን ስሪት መርቼዲስ አውቶቢስ

800,000.00 መስከረም 25/2015 3፡00- 4፡30

አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን የድርጅቱ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ሀራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል ፡፡

 

ተ.ቁ

 

የንብረቱ ዓይነት

 

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

 

የንብረቱ

መገለጫ

የጨረታው

መነሻዋጋ

ብር

ሐራጁ የሚካሄድበት
ቀን ሰዓት
5  አጋር ማይክሮ ፋይናን አ/ማ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረድ ብሎ ጎጆ ሆቴል ጀርባ በሚገኘው የኩባንያው በዕዳ የሚያዙ ተሸከርካሪዎች ማቆያ ጊቢ ውስጥ ሠ.ቁ አአ 03-25974

የተሰራበት ዘመን 1990 ዓ.ም ቶዮታ ኮሮላ

300,000.00 መስከረም 25/2015 7፡30

8፡30

6 አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረድ ብሎ ጎጆ ሆቴል ጀርባ በሚገኘው የኩባንያው በዕዳ የሚያዙ ተሸከርካሪዎች ማቆያ ጊቢ ውስጥ ሠ.ቁ አአ 03-64940

የተሰራበት ዘመን 1991 ዓ.ም ሱዚኪ ቪታራ

300,000.00 መስከረም 25/2015 8፡30

9፡30

ማሳሰቢያ

 1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ኛ ወይም (25)በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) በኩባንያው ስም አሰርቶ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፤
 2. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን አንስቶ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ አጠቃሎ በመክፈል ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሱት ቀናት ቀሪውን ክፍያ አጠናቆ ከፍሎ ንብረቱን ባይረከብ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ ለጨረታ ያስያዘውም ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ተደርጐ በንብረቱ ላይ በድጋሚ ጨረታ ይወጣል፡፡
 3. የንብረቱ ስመ ሀብት ወደ ገዥ እንዲዞር ኩባንያው ሰነዶችን ያስረክባል ፤ለሚመለከተው መንግስታዊ አካልም ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
 4. ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ፡- በተራ.ቁጥር ከ1 እስከ 3 ላይ የተጠቀሰው ተሸከርካሪ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረድ ብሎ ጎጆ ሆቴል ጀርባ በሚገኘው የኩባንያው በዕዳ የሚያዙ ተሸከርካሪዎች ማቆያ ጊቢ ውስጥ ነው ፡፡ ተራ ቁጥር 4 ላይ የተጠቀሰው ተሸከርካሪ በኦሮሚያ ልዩ ዞን አቃቂ ወረዳ ዱከም ከተማ እንዲሁም የድርጅቱ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች  በተ.ቁ 5 እስከ 6 ላይ የተጠቀሱትን ተሸከርካሪ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረድ ብሎ ጎጆ ሆቴል ጀርባ በሚገኘው የኩባንያው በዕዳ የሚያዙ ተሸከርካሪዎች ማቆያ ጊቢ ውስጥ ነው ፡፡
 5. ለሐራጅ የቀረቡትን ንብረቶች መጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ዘወትር  በስራ ሰአት አስቀድሞ ፕሮግራም በማስያዝ በሚሰጠው ቀጠሮ መሰረት መጎብኘት ይችላል::
 6. የስም ማዛወሪያን ጨምሮ ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ማንኛውንም ክፍያ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል፡፡
 7. በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ተወካዮች እና የንብረቱ ባለቤቶች ብቻ ናቸው፡፡
 8. ጨረታን የሚመለከቱ ደንብና መመሪያዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

ዋና መ/ቤት ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ ዳማ ሀውስ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302፣307፣309፣310 ዘወትር በስራ ሰዓት በግምባር ቀርቦ መጠየቅ ወይም በስልክ ቁጥሮች 011-5-57-82-32 (ኦፕሬሽን መምሪያ)፣ 011-5-57-72-32 ( ኦፕሬሽን መምሪያ)፣ 011-4-71-86-97 (ዱከም ቅ/ፍ) 011-5-51-69-44 (ቂርቆስ ቅ/ፍ )፤ 011-2-77-05-67( ኮልፌ ቅ/ፍ) በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማ