አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማ የባለአክሲዬኖች የ18ኛ መደበኛ እና 12ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤው

Announcement
Aggar-Micro-Finance-logo-1

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 09/29/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/29/2022

Description

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ

አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማ የባለአክሲዬኖች የ18ኛ መደበኛ እና 12ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ቅዳሜ ጥቅምት 19 ቀን 2015ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በራስ ሆቴል አዳራሽ ያካሂዳል፡፡

የ18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች:-

 1. የጉባኤውን ፀሐፊ መምረጥ
 2. ድምጽ ቆጣሪዎችን መሰየም
 3. ምልአተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ
 4. የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ
 5. ለነባርና አዳዲስ ባለአክሲዮኖች የተሸጡትን አክሲዮኖች እና የአክሲዮን ዝውውሮች ማጽደቅ
 6. የዳይሬክተሮች ቦርድን ሪፖርት ማድመጥ
 7. የውጪ ኦዲተር ሪፖርት ማድመጥ
 8. በሁለቱ ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን
 9. በአመቱ በተገኘው ትርፍ ላይ ተወያይቶ መወሰን
 10. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን አበል መወሰን
 11. የዳይሬክተሮች ቦርድን አባላት አስመራጭ ኮሚቴ መምረጥና መሰየም
 12. የዳይሬክተሮች ቦርድን ምርጫ ማካሄድ
 13. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ ናቸው፡፡

የ12ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፡-

 1. ድምጽ ቆጣሪዎችንና ጸኃፊ መሰየም
 2. ምልአተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ
 1. አጀንዳ ማጽደቅ
 2. ባልተሸጠው አክሲዮን ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ
 3. የኩባንያውን ካፒታል ማሳደግ
 4. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ ናቸው፡፡

ስለሆነም ሁሉም ባለአክሲዬኖች ከላይ በተጠቀሰው እለት እና ቦታ እንዲገኙ ኩባንያው ጥሪ እያቀረበ መገኘት የማይችሉ በንግድ ሕግ ቁጥር 402 መሠረት ጉባኤው ከመካሄዱ 3 ቀን ሲቀረው ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ ዳማ ሐውስ ህንጻ ላይ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 306 በአካል ቀርበው በድርጅቱ የተዘጋጀውን የውክልና ፎርም በመሙላት ተወካይ እንዲሰይሙ ያሳስባል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም ባለአክሲዬኖች ማንነታቸውን የሚገልፅ የታደሰ ቀበሌ መታወቂያ፣ ፖስፖርት ወይም መንጃፍቃድ እና ተወካይ የውክልናውን ዋናውንና ኮፒውን ይዘው እንዲቀርቡ በአክብሮት ያሳስባል፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ