አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ ከታች በሰንጠረ¡ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፣

Agri-Service-Ethiopia-Logo-ReporterTenders

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 10/26/2021
 • Phone Number : 0114666417
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/06/2021

Description

አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ አዲስ አባባ ዋና መ/ቤት የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ፣

አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ ከታች በሰንጠረ¡ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፣

ቁጥር   ዝርዝር
1 ያገለገሉ ጀኔሬተሮች በቁጥር ሁለት
2 የቶዮታ ተሽከርካሪ መለዋወጫ ከተ.ቁ 1-29
3 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች ከተ.ቁ 1-14
4 ያገለገሉ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣  ካሜራ፣ ላፕቶፕ፣ ፐሮጄክተር
5  ያገለገሉ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተርና ሌሎች
6 ወንበሮች፣ ሸልፎች፣ ጠረጴዛዎችና ሌሎች ዕቃዎች
7 ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች
8 ያገለገለ ሞተር ሳይክል
 1. የዕቃዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ከአግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ ዋናው መ/ቤት አስተዳደር ክፍል የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ  ብር/ በመክፈል  ከጥቅምት  18 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ድረስ  መውሰድ ይቻላል፡፡
 2. የዕቃዎቹ አይነትና ዝርዝር ከአግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ ዋናው መ/ቤት፣ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 9፡00 በአካል በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
 3. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡትን ዕቃዎች በመለየትና ዋጋ በመስጠት መጫረት ይኖርባቸዋል፣
 4. ተጫራቾች የሚገዙትን ዕቃ አይነትና ዋጋ በመግለጽ በፖስታ አሽገው የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2014 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ 7% /ሰባት በመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሲፒኦ ያልቀረበበት እና በጨረታው ሰነድ ላይ የተቀመጠውን መሰፈርት የማያሟላ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
 6. ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
 7. ጨረታው የሚከፈዉ ጥቅምት 29 ቀን 2014 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡
 8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 9. ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች በ5 ቀናት ውስጥ ሙሉ ገንዘብ ክፍሎ ዕቃውን ማንሳት ይኖርበታል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጽያ

ግሉባል ሆቴል በስተጀርባ፣ አዲስ አበባ

ስልክ ቁጥር 0114-666417፣0114-651212

Send me an email when this category has been updated