አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ የበቆሎ ዱቄት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

Agri-Service-Ethiopia-Logo-ReporterTenders-3

Overview

 • Category : Agriculture Farm Products
 • Posted Date : 03/28/2021
 • Phone Number : 0114651212
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/06/2021

Description

የበቆሎ ዱቄት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን በደቡብ ብ/ቤ/ህ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ኦሞ ዳሰነች ወረዳ ጽ/ቤት በሚገኘዉ የአርብቶ አደር ቀበሌዎች በመሰራት ላይ ከሚገኘዉ የዘላቂ ልማት ፕሮጄት በተጨማሪ ፈጣን ደራሽ እርዳታዎችን ጎን ለጎን በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡ በመሆኑም 861 ኩንታል የበቆሎ ዱቄት በ50 ኪሎ ግራም የታሸገ ሆኖ የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜ ረጅም ያለ እና ጥራቱ የጠበቀ ዱቄት አወዳድሮ  ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚጠበቅባቸዉ፡-

 1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና ንግድ ምዝገባ ያላቸው፡፡
 2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይ መለያ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 3. የጨረታ ማስከበሪያ 1% በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታው ሠነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
 4. የዘመኑን ግብር አጠናቆ ለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
 5. ተጫራቾች የግዥውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል አዲስ አበባ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጎተራን ማሳለጫን ከፍ ብለዉ ግሎባል ሆቴል ጀርባ ከሚገኘው ከድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት ከእሮብ መጋቢት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስታወቂያዉን በመመልከትና ሰነዱን በመግዛት ከታች በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 7. አሸናፊው ውል ከገባ በኋላ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አያደርግም፡፡
 8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ

ግሎባል ሆቴል በስተጀርባ

አዲስ አበባ

ስልክ ቁጥር 0114-666417/0114-651212

Send me an email when this category has been updated