አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ የጥበቃ፣ የጽዳትና አትክልተኛ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን አወዳድሮ ውል በመፈጸም አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል፡፡

Agri-Service-Ethiopia-Logo-ReporterTenders-1

Overview

  • Category : Labor Supply Service
  • Posted Date : 01/10/2023
  • Phone Number : 0114666417
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/19/2023

Description

  አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ

የጥበቃ አገልገሎት ማስታወቂያ

አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያለሆነ አገር በቀል የልማት ድርጅት ነዉ፡፡ ድርጅቱ የጥበቃ፣ የጽዳትና አትክልተኛ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን አወዳድሮ ውል በመፈጸም አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ለቀን 2 እና ለምሽት 3 የጥበቃ ሠራተኞችን በአጠቃላይ 5 የጥበቃ ሰራተኞችን እንዲሁም አንድ የጽዳት ሰራተኛ እና አንድ አትክልተኛ ለማሰማራት ከሚችል ድርጅት ጋር ውል በመፈጻም አገልግሎቱን ማገኘት ይፈልጋል፡፡ ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚገባቸዉ፤

  1. የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ ታክስና የተ.እ.ታ ሰርቲፊኬት፣
  2. የድርጅቱ ካምፓኒ ፕሮፋይል፣
  3. የአገልግሎች ክፍያ ዋጋ ማቅረብ፣
  4. የስራ ልምድን የሚገልጽ ማስረጃዎች፣
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 5000 (አምስት ሺ) ከባንክ ማሰራት ይጠበቅበታል

 

ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል ከማክሰኞ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ሰነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡የጨረታ ማስገቢያ ቀን ጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ሲሆን የጨረታ መክፈቻ  ቀን ጥር 11 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ነዉ፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ቴክኒካል እና የፋይናንሻል በመለየት ኦሪጂናል እና ኮፒ በፖስታ ላይ በመለጠፍ አድራሻን በመጻፍና በማሸግ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

አድራሻ፡ አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵና ዋና ጽ/ቤት ግሎባል ሆቴል ጀርባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 2 የቤት ቁጥት 397 የሰዉ ሃብትና ንብረት አስተዳደር መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114-666417/ 0114-651212 መደወል ይቻላል